ሁዋዌ በምዕራባውያን ሀገሮች የሚደርስበትን ወቀሳ አጣጣለ

የቻይናው ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያ ሁዋዌ ከደህንነት ችግር ጋር በተያያዘ ከምዕራባውያን ሀገሮች የሚደርስብትን ቅሬታ ውድቅ አድርጓል።

ኩባንያው በአሜሪካና በሌሎች ሀገሮች የተለያዩ የደህንነት ስራዎችን ከተለያዩ አካላት ጋር በመመሳጠር ይሰራል በሚል የተለያዩ ቅሬታዎች እየቀረቡበት ይገኛሉ።

ይህን ተከትሎም የምዕራባውያን ሀገሮችና ቻይና በጉዳዩ ዙሪያ የሚያደርጉት እሰጣ ገባ ቀጥሏል።

ከትቂት ቀናት በፊት የሁዋዌ ኩባንያ መስራችና ባለቤት ልጅ የሆነቸው ሜንግ በካናዳ ፖሊስ በቁጥጥ ስር በመዋል ከቀናት ቆይታ በኋላ  በዋስ መፈታቷ ይታወሳል።

አዎስትራሊያና ኒውዚላንድ የሁዋዌ ሞባይል 5ጂ ኔትዎርክ ከደህንነት ችግር ጋር በተያዘ በሀገር ውስጥ አገልግሎት እንዳይሰጥ አግደዋል።

ይሁን እንጂ ሁዋዌ አውሮፓውያኑ የሚያነሱትን ቅሬ በመረጃ ላይ ያልተመሰረተ መሰረተ ቢስ ውንጀላ ሲል አጣጥሎታል ።

ሀገራቱ እንደሚሉት በኩባንያው ላይ የደህንነት ስጋት ኖሯቸው ሳይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ የድርጅቱን ተቀባይነት ለማሳጣት የሚደረግ አሻጥር ነው ብሏል።

ከዚህ ባለፈም ሀገራቱ በቻይና እየተፈጠረ ያለውን የቴክኖሎጂ ፈጠራ በማስተጓጎል ሀገሪቷ ከዓለም የገበያ ውድድር እንድትወጣ የሚያደርጉት አጉል ሙከራ መሆኑን ገልጿል።

ስለሆነም ሀገራቱ ያለምንም ማስረጃ ድርጅቱን ከመውቀስ እንዲቆጥቡ በማሳሰብ ፥ምርቱ ከምንም ዓይነት የደህንነት ስራ ውስጥ የማይሳተፍ መሆኑን ለማሳየት ፈቃደኛ መሆኑን አሳውቋል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.