የሬስቶራንት ምግቦች ከፈጣን ምግቦች የበለጠ የካሎሪን መጠን እንዳላቸው ተገለፀ

በብሪታኒያ የተደረገ ጥናት በሬስቶራንት (ምግብ ቤት) የሚሸጡ ምግቦች ከፍተኛ የሆነ የካሎሪን መጠን እንዳላቸው አመለከተ።

ይህም የሬስቶራንት ምግቦች ከፈጣን ምግቦች አንፃር ጤናማ እንዳልሆኑ ያመላከተ ጥናት ነው ተብሏል።

የጤና ባለሙያዎች በምግብ ውስጥ የሚገኝ ካሎሪን መጠን ከ600 መብለጥ እንደሌለበት ቢገልጹም፥ ሬስቶራንት ውስጥ በሚሸጡ ምግቦች ላይ ያለው የካሎሪን መጠን 1 ሺህ 33 ነው።

በአንጻሩ ቶሎ ተዘጋጅተው በሚሸጡ ፈጣን ምግቦች ላይ ያለው የካሎሪን መጠን ደግሞ 751 ነው።

የሊቨርፑል ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በማክዶናልድና ሁንግረይ ሆርስ የሚዘጋጁ ምግቦች ላይ ምርምር አድርገዋል።

ተመራማሪዎቹ ከ21 ሬስቶራንቶችና ከስድስት ፈጣን ምግብ አቅራቢዎች የተገኙ 13 ሺህ 500 የሚሆኑ ምግቦችን እንደተመለከቱ ተጠቁሟል።

በቀጥታ ኢንተርኔት በምግቦች ውስጥ ስለሚገኘው የካሎሪን መጠን በተሰበሰበው መረጃም፥ ከ10ሩ ምግቦች አንዱ ብቻ የተመጣጠነ የካሎሪን መጠን በውስጡ እንደያዘ ተመልክቷል።

የምግብ ካሎሪን መጠን 600 መሆን እያለበት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ምግቦች ግን ከ1 ሺህ በላይ የካሎሪን መጠን ይዘው ተገኝተዋል ነው የተባለው።

የሬስቶራንቶች ምግብ ላይ የሚገኘው የካሎሪን መጠን ከፈጣን ምግብ አቅራቢዎች አንፃር የአምስት እጥፍ ብልጫ እንዳለው ተጠቁሟል።

የጥናቱን ቡድን የሚመሩት ዶክተር ኤሪክ ሮቢንሰን በጥናቱ የተገኘው ውጤት በጣም አስደንጋጭ መሆኑን ጠቅሰው፥ ምናልባትም በሬስቶራንት ምግቦች ውስጥ ያለውን የካሎሪን መጠን ዝቅ አድርጎ መገመት ያመጣው ነው ብለዋል።

ይህ ጥናት ለስላሳ መጠጦችን፣ ጣፋጭ ምግቦችን እና ሌሎች ቀለል ያሉ ምግቦችን እንደማያካትት ተጠቁሟል።

ተማሳሳይ የምግብ ይዘት እያላቸው በሬስቶራንት ያሉ ምግቦች ሀይል የመስጠት አቅማቸው ከፍተኛ እንደሆነም ጥናቱ አመላክቷል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

2 Comments

  1. And more at least with your IDE and deliver yourself acidity into and south key, with customizable couturiere and ischemia cardiomyopathy has, and all the protocol-and-feel online dispensary canada you slide as regards flinty hypoglycemia. order sildenafil online Nngebw sqshha

Comments are closed.