ቸል ሊባሉ የማይገባቸው የኤች አይ ቪ ምልክቶች

የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ ምልክቶች አንዳንድ ጊዜ ለረጅም ጊዜ ሊደበቁ ይችላሉ።
ይሁን እንጂ ቫይረሱ ወደ ሰውነታችን ከገባ ከ1 እስከ 2 ወራት ባሉት ጊዜያት ውስጥ 50 በመቶ የኤች አይ ቪ ኤድስ ተጠቂዎች በቅድሚያ የሚገጥማቸው የህመም ምልክቶች (አኪዩት ሪትሮቫይራል ሲንዱረም) አሉ።
እነዚህ የህመም ምልክቶችን ካስተዋልን ታዲያ ኤች አይ ቪ ፖዘቲቭ ልንሆን ስለምንችል ወደ ህክምና ተቋማት ማምራት ተገቢ ነው ፡፡
ኤች አይ ቪ ልቅ በሆነ የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ የደም ንክኪ፣ ስለታማ ነገሮችን በመጋራት እንዲሁም በእርግዝና ወቅት ከእናት ወደ ልጅ እንደሚተላለፍ ይታወቃል።
እርግጥ ነው በርካቶቻችን ስለ ኤች አይ ቪ ኤድስ ያለን ግንዛቤ አነስተኛ ነው የሚባል ባይሆንም ከዚህ በታች የዘረዘሩት ግን ምናልባትም የሌላ ህመም ምልክቶች ናቸው በሚል ቸል እያልናቸው ለሞት ሊዳርጉን ስለሚችሉ ብናስተውላቸው መልካም ነው።
1. ትኩሳት
ትኩሳት የመጀመሪያው የኤ አር ሲ ምልክት ሲሆን፥ ከጉሮሮ ህመም፣ ከሊምፍ (በደም ውስጥ የሚገኝ ፈሳሽ ንጥረ ነገር) አመላላሽ ቱቦዎች እብጠት እና ከድካም ጋር ይያያዛል።
2. ከፍተኛ የድካም ስሜት
ሰውነታችን በኢንፌክሽን (ማመርቀዝ) ሲዳከም የመቆጣት ምላሽ ይሰጣል። ይህም ለህመሞች የሚሰጠው ምላሽ ከፍተኛ የድካም ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል።
3. የመገጣጠሚያ አጥንቶች ህመም
4. የጉሮሮ ህመም እና ከፍተኛ የራስ ምታት
5. የቆዳ መንደብደብ
6. ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ እና ተቅማጥ
ከ30 እስከ 60 በመቶ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ለአጭር ጊዜ የሚቆይ የተቅማጥ በሽታ ያጋጥማቸዋል።
7. ክብደት መቀነስ
8. ደረቅ ሳል ፡- ለሳምንታት የዘለቀ ደረቅ ሳልም በቫይረሱ መያዝን ሊያመላክት ይችላል።
9. የሳንባ ኢንፌክሽን
10. የሌሊት ላብ ፡- ግማሽ የሚሆኑት የኤች አይ ቪ ኤድስ ተጠቂዎች በሌሊት ላብ ይጠቃሉ።
11. የጥፍር ቀለም እና ቅርፅ መቀየር ፡- የጥፍሮች መታጠፍ እና መጥቆር ቫይረሱ ወደ ሰውነታችን እንደገባ ሊታዩ ይችላሉ።
12. የመተንፈሻ እና የመራቢያ አካላት ህመም
13. መንቀጥቀጥ ፤ የእግር እና እጅ ጡንቻዎች መልፈስፈስ
14. የወር አበባ ኡደት መዛባት

ማንኛውም ኤች አይ ቪ ን በተመለከተ እንዲሁም ሌሎች የጤና ጉዳዮችን ማዋየት ከፈለጉ 8809 የዶክተር አለሀኪሞች ጋር ደውለው ማማከር ይችላሉ፡፡

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

4 Comments

Comments are closed.