ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ከተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ሊ ዮንግ ጋር ተገናኝተው ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዋና ዳይሬክተሩ ጋር ያደረጉት ውይይት በዋናነት በኢትዮጵያ ውስጥ የተቀናጀ የግብርና ኢንዲስትሪ ፓርኮችን ለማጠናከር የድርጅቱ ድጋፍ ቀጣይነት ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩና የዋና ዳይሬክተሩ ውይይት ረፋድ ላይ መካሄዱን ተገልጿል፡፡

የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮች የግብርና ምርታማነትን በማረጋገጥ እሴትን በመጨመርና የኢትዮጵያዊያንን ኑሮ በማሻሻል የሀገሪቱን ኢኮኖሚ መዋቅር ያሸጋግራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.