የህግ ባለሙያዋ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አዲስ አበባ ገቡ

የህግ ባለሙያዋ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በዛሬው እለት አዲስ አበባ ገብተዋል።

በአሜሪካ ሲኖሩ የነበሩት የህግ ባለሙያዋ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬ ማለዳ ነው አዲስ አበባ የገቡት።

ከሰባት ዓመት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ወደ ሀገር እንዲለመሱ ያነሳሳቸውን ነገር ሲናገሩም፥ በኢትዮጵያ የተጀመረውን የዴሞክራሲ እንቅስቃሴ ለማገዝ እንዲያስችል ታልሞ የተፈጠረው ዕድል ነው።

አሁንም በሀገሪቱ እየተፈጠረ ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ለፍትህ መስፈን የበኩላቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል።

ወይዘሪት ብርቱካን በፌደራል ፍርድ ቤት ዳኛ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን፥ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ መስራች የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል።

ለዴሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት መከበር ላደረጉት አስተዋጽኦም ዓለም አቀፍ ሽልማት አግኝተዋል ።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.