መሃጸን ውስጥ የሚቀመጡ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች በመሃጸን ጫፍ ካንሰር የመያዝ እድልን ሊቀንሱ ይችላሉ

መሃጸን ውስጥ የሚቀመጡ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች በመሃጸን ጫፍ ካንሰር የመያዝ እድልን ሊቀንሱ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

በካሊፎርኒያ የጤና ተመራመሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በ12 ሺህ ያህል እናቶች ላይ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ማህጸን ውስጥ የሚቀመጡ የወሊድ መከላከያ ዘዴዎችን የሚጠቀሙ እናቶች በማህጸን ጫፍ ካንሰር የመጠቃታቸው ምጣኔ ዝቅ ብሎ መታየቱ ተነግሯል።

የማህጸን ጫፍ ካንሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ በተስፋፊነቱ 3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፥ በተለይም በታዳጊ ሀገራት ላይ ከፍተኛ ተስፋፊነት ያለው መሆኑም ተመላክቷል።

ለዚህም በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የዘርፉ ህክምና ዘዴዎች ውስንነት በምክንያትነተ ተጠቅሷል።

በዳሰሳ ጥናቱ አበረታች ውጤት መታየቱን የተናገሩት የጥናቱ ጸሃፊ ማህጸን ውስጥ የሚቀመጡ የወሊድ መከላከያዎች እናቶችን ከማህጸን በር ጫፍ ለመከላከል የሚያስችሉ ሁኔታዎችን እንደፈጠሩላቸው ጠቁመዋል።

የዳሰሳ ጥናቱ ውጤት ከላይ የተጠቀሱት የወሊድ መቆጣጠሪያወቆች ከቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ባለፈ ከመሃጸን ካንሰር ተጋላጭነት ለመጠበቅ የሚያስችሉበት ሁኔታ ላይ ጥናት ለማድረግ በር ከፋች ነው ተብላል።

የዓለም የጤና ድረጅት መረጃ እንደሚያመላክተው በፈረንጆቹ 2012 በዓለም አቀፍ ደረጃ 528 ሺህ እናቶች የማህጸን ጫፍ ካንሰር ህክምና የተደረገላቸው ሲሆን፥ ከህሙማኑ መካከል 266 ሺህ ያህሉ ህይወታቸው አልፏል።

ከላይ የተጠቀሰው አሃዝ በ2035 ላይ 756 ሺህ እንደሚደረስ እና ለ416 ሺህ ያህል እናቶች የሞት መንስኤ ሊሆን፥ እንደሚችልም መተንበዩንም ነው ዘገባው የሚያመላክተው።

ተመራመሪዎቹ የወሊድ መቆጣጠሪያዎቹን ተጠቃሚ የሆኑ እናቶች በማህጸን ጫፍ ካንሰር የመጠቃታቸው ምጣኔ እንዴት ሊቀነስ እንደቻለ የተለያዩ መላምቶችን የሰነዘሩ ቢሆንም፥ ተጨማሪ ጥናቶችን ማካሄዱ ጠቃሚ መሆኑንም ዘገባው ያስረዳል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.