ቬትናም የማህበራዊ ሚዲያዎችን አጠቃቀም የሚቆጣጠር ህግ ልታፀድቅ ነው

ቬትናም የማህበራዊ ሚዲያዎችን አጠቃቀም የሚቆጣጠር የሳይበር ሕግ ልታፀድቅ መሆኑን የሀገሪቱ የደህንነት ሚኒስትር አስታውቋል ።

ይህ የሳይበር ሕግም በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ ሀሰተኛ መረጃዎችን ፣የሽብር ድርጊቶችንና መሰል ተግባራትን ለመቆጣጠር ያስችላል ተብሏል።

ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች በሀገራቸው ያለውን የስራ ፈጠራ ሁኔታን ከማበረታታት ይልቅ ሀገራቸውን የደህንነት ስጋት ውስጥ እየከተቱ በመሆኑ ፥ድርጊቱን ለመከላከልም የሳይበር ህግ ማውጣት ተገቢ መሆኑን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የሀገሪቱ ህግ አውጪ አካላት በበኩላቸው ፥ በማህበራዊ ሚዲያዎች በተለይም በፌስብክና ጎግል አይነት መተግበሪያዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የአጠቃቀም ህግ ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ማህበራዊ ሚዲያዎችን ተጠቅመው የሀገሪቱን መንግስተና ዜጎች መረጃ የሚመዘብሩ አካላትን ለመቆጣጠርም የሳይበር ሕጉ ሁነኛ መፍተሄ ነው ተብሏል።

ሰለሆነም የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነት ለማስጠበቅ የሳይበር ሕጉ በሚቀጥለቀው ዓመት ተግባራዊ እንደሚሆን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ይህ ህግም በቬትናም በስፋት አግልግሎት ላይ የዋሉት ፌስቡክና ጎግል በሀገር ውስጥ ተጠሪ መስሪያ ቤት እንዲከፍቱ የሚያስገድድ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም ድርጅቶቹ የተጠቃሚዎችን መረጃ በተገቢ ሁኔታ የማስቀመጥና አላስፈላጊ መረጃዎችን የማስወገድ ሃላፊነትም ይሰጣቸዋል ነው የተባለው።

የሳይበር ሕጉ ዜጎች የማህበራዊ ሚዲያን እንዳይጠቀሙ የሚያግድ ሳይሆን ህጉንና ደንቡን ተከትለው በስርዓት እንዲጠቀሙ የሚያስችል ነው ተብሏል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.