በአሜሪካ ምርጫ ዲሞክራቶች የምክር ቤት መቀመጫዎችን የተቆጣጠሩ ሲሆን ይህም ትራምፕን አስደንግጧል

በአሜሪካው “ሚድ-ተርም” ምርጫ ዲሞክራቶች 435 የሕዝብ እንደራሴዎች ያሉትን ምክር ቤት (ሀውስ ኦፍ ሪፕረዘንታቲቭስ) ማሸነፋቸው እየተዘገበ ነው። ይህም ለሪፓብሊካኑ ትራምፕ ትልቅ ሽንፈት ነው።

ዲሞክራቶች የታህታዩ ምክር ቤት (ሀውስ ኦፍ ሪፕረዘንታቲቭስ) ከስምንት ዓመታት በኋላ ማሸነፍ መቻላቸው የፕሬዚዳንቱን አጀንዳዎች እንዳሻቸው መቀያየር ያስችላቸዋል።

በሌላ በኩል 100 አባላት የሚኖሩትን የሴኔቱን ምርጫ ሪፐብሊካኖች እንደሚያሸንፉት ተገምቷል።

የ”ሚድ-ተርም” ምርጫ ምንድነው?

‘ሚድ-ተርም’ የተባለው መሀል ላይ ስለሚካሄድ ነው። ለአራት ዓመት እንዲያገለግል የተመረጠው ፕሬዚዳንት ሁለት ዓመት እንደቆየ የሥራ ዘመኑ ይጋመሳል። በዚህ ወቅት “ሚድ-ተርም” ምርጫ ይከሰታል። ምርጫው ታዲያ በአራት ዓመት አንድ ጊዜ በወርሃ ኖቬምበር (ኅዳር) ነው የሚካሄደው።

ምን ዓይነት ምርጫ ነው?

የአሜሪካ ምክር ቤት ላዕላይና ታህታይ ምክር ቤቶች አሉት። ታህታዩ ምክር ቤት 435 የሕዝብ እንደራሴዎች ሲኖሩት ‘ሀውስ ኦፍ ሪፕረዘንታቲቭስ’ ይባላል፤ ላዕላዩ ምክር ቤት 100 አባላት ሲኖሩት ተመራጮቹ ሴናተሮች ተብለው ይጠራሉ።

የኅብረት ስማቸው ኮንግረስ ነው። ይህ ሕግ አውጪ ምክር ቤት በድምሩ 535 አባላት ይኖሩታል። በደፈናው አንድ ረቂቅ ሕግ ከላዕላዩም ከታህታዩም ምክር ቤት ሊመነጭ ይችላል ማለት እንችላለን።

የዘንድሮ ምርጫ ለምን አጓጊ ሆነ?

ምርጫ በዶናልድ ትራምፕ ላይ የሚካሄድ ሕዝበ ውሳኔ ተደርጎ ተወስዷል። ለምን?

አንዱ ምክንያት ሁለቱም የምክር ቤት ወንበሮች በሪፐብሊካን ወኪሎች አብላጫ ተይዘው መቆየታቸው ነው። የዚህ ምርጫ ውጤት ግን የሚያሳዩት ወንበሮቹ ከሪፐብሊካን እጅ እንደወጡ ነው። ይህ ማለት ትራምፕ ለትራምፕ ትልቅ ሽንፈት ነው። ዶናልድ ትራምፕ ውሳኔዎቻቸውን ለማጸደቅ ምጥ ይሆንባቸዋል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.