‘‘ፍልክስፔይ’’ የተባለ ታጣፊ ዘመናዊ የእጅ ስልክ ለገበያ ሊቀርብ ነው

‘ፍልክስፔይ’’ የተባለ ታጣፊ ዘመናዊ የእጅ ስልክ ለገበያ ሊቀርብ መሆኑ ተገልጿል።

አዲሱ ታጣፊ ስልክ ሲዘረጋ 19ነጥብ8 ሴንቲ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን፥ አሁን ላይ በአገለግሎት ላይ ካሉት ታፕሌቶች ሁሉ ባለ ሰፊው ስክሪን ነው ተብሏል።

ስልኩ ከ3 የሚታጠፍ ሲሆን፥ የፊት፣ የጀርባ እና የጎን ጠርዝ እስክሪኖች እንዳሉትም ታውቋል።

የዚህን አዓይነት ቴክኖሎጂ ውጤት ሳምሰንግ ወይንም ሁአዌ ለገበያ ያቀርባሉ ተብለሎ ሲጠበቅ ከተመሰረተ ገና 6 ዓመት የሆነው ሮዮል የተባለው የቻይና ኩባንያ ምርቶቹን ለገበያ ሊያቀርብ መሆኑ የዘርፉ ኩባንያዎችን አስገርሟል ተብሏል።

አዲሱን የተጣጣፊ ስልክ ቴክኖሎጂ በቤጅንግ በተካሄደ ዝግጅት ላይ ይፋ ያደረገው ኩባንያው ከዛሬ ጀምሮ ወደ ምርት እንደሚሸጋገር ነው በዘገባው የተመላከተው።
በሚቀጥለው ወርም ለገበያ አንደሚቀርብ ተነግሯል።

ስልኩ በተለያዩ ‘‘ስፔስፊኬሽኖች’’ እና የሚሞሪ መጠን ለገበያ የሚቀርብ ሲሆን፥ ከ1 ሺህ290 እስከ 1ሺህ863 ያህል የአሜሪካን ዶላር ዋጋ እንደሚቆረጥለትም ነው የተገለጸው።

ቀደም ሲል ተቀማጭነቱን በካሊፎርኒያ ያደረገ ኩባንያ የመጀመሪያ ታጣፊ ስማርት የእጅ ስልክ መስራቱን ይፋ ማድረጉን ዘገባው አስታውሷል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.