ለወዛም ፊት የሎሚ ጭማቂ

ሎሚ የፊታችን ቆዳ በጣም ወዛምና ቅባታማ ከሆነ ወዛችን እንዲቀንስ ይረዳናል፡፡ በተጨማሪም አይናችን ዙሪያ እና አገጫችን እንዲፀዳ ያደርጋል፡፡
አጠቃቀም፡-1
አንድ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ ከግማሽ የሻይ ማንኪያ ውሀ ጋር በመደባለቅ በንፁህ ጥጥ እየነከርን የፊታችንን ቆዳ መቀባት፡፡ ከ10 ደቂቃ ቡኃላ ለብ ባለ ውሀ መታጠብ ወዝ ለሚበዛበት የፊት ቆዳ የተመጣጠነ ወዝ እንዲኖረው ያደርጋል፡፡
አጠቃቀም፡-2
አንድ የሻይ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ፤ አንድ የሻይ ማንኪያ የሎሚ የወተት ዱቄት1/2 አንድ የሻይ ማንኪያ ማር ሁሉንም አንድ ላይ በማደባለቅ ፊታችን ላይ መቀባት ከ 10-15 ደቂቃ አቆይቶ በቀዝቃዛ ውሀ መታጠብ፡፡
ፊታችን እንዲፀዳና የተስተካከለ የፊት ወዝ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡
በየቀኑ ከተጠቀምን በሣምንት ውስጥ ውጤቱን ማየት እንችላለን

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

9 Comments

Comments are closed.