ትኩስ ቡና ከቀዝቀዛ ቢራ ይልቅ የተሻለ ነው

ጆርናል ሳይንቲፊክ ሪፖርት በተባለው የምርምር መጽሔት ላይ የታተመ አንድ አዲስ ጥናት እንዳተተው ከሆነ ትኩስ ቡና መጠጣት ቀዝቃዛ ቢራ ከመጠጣት ይልቅ ጠቃሚ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡

የመጀመሪያ ነው በተባለውና በዚህ በንጽጽር በተሰራው ምርምር የተሳተፉት በፊላደልፊያ የሚገኙ ኬሚስቶች እና ቶማስ ጀፈርሰን ዩኒቨርስቲ ናቸው ተብሏል፡፡

ከንጽጽር ሂደቶቹ መካከልም ቡና ለመፍላት ወይንም ለመዘጋጀት አጭር ጊዜ እንደሚወስድ ጠቅሰው ቢራ በአንጻሩ ከሦስት ሰዓታት እስከ አንድ ቀን እንደሚፈጅ አንስተዋል፡፡

በዚህም ቡና ለመዘጋጀት የሚወስደው ጊዜ ማጠር ኦክስጅን እንዲሰራጭ የሚያደርገውን ቲትራተብል የተሰኘውን አሲድ እንዲይዝ ያደርገዋል ሲሉ ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ቡና አንቲኦክሲዳንት እንዳለውም የጠቀሱ ሲሆን፥ ይህም የሰውነታችንን ህዋስ ከአደጋ ይጠብቃል፤ እንዲሁም የሲጋራ ጢስና መሰል ጉዳዮች ወደ ሰውነት በሚገቡበት ወቅትም ይከላከላል ብለዋል፡፡

ተመራማሪዎች ከቀዝቃዛ ቡና ይልቅ ትኩስ ቡና መጠጣቱም የተሻለ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል፡፡

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.