ክሮም የተባለ የጥርስ ማስዋቢያ ቀለም ገብያ ላይ ዋለ

ክሮም የተባለው የጥርስ ማስዋቢያ ቀለም ገበያ ላይ ውሏል።

የጥርስ ማስዋቢያ ቀለሙ በ10 የተለያዩ ቀለማት አማራጭ ለገበያ የቀረበ ሲሆን፥ አንድ ጊዜ ከተቀቡት ሳይለቅ እስከ 24 ሰዓት እንደሚቆይም ተነግሯል።

ቀለሙ ከጸጉር ቀለም፣ አልባሳት፣ የጥፍር ቀለሞች እና ከሰዎቹ አጠቃላይ ሁኔታ ጋር የሚሄዱ ቀለሞችን በመምራጥ ለመጠቀም እና ጥረስን ለማስዋብ ያስችላል ተብሏል።

በዚሁ የጥርስ ቀለም የተዋቡ ሰዎች ማንኛውንም የምግብ አይነት መመገብ የሚችሉ ሲሆን፥ ምንም አይነት ቃና የሌለው እና ጥርስን የማይጎዳ መሆኑን የጥርስ ቀለሙን የቀመመው ኩባንያ አስተውቋል

አስፈላጊ በሆነ ጊዜም በቀላሉ በጥረስ ሳሙና እና ውሃ ለማስለቀቅ እንደሚቻልም ተጠቁሟል።

ስለሆነም በየትኛውም የጤና ሁኔታ እና የስራ አካባቢ በቀላሉ ለመጠቀም የሚቻል መሆኑን ነው የክሮም ጥርስ ቀለሙ የፈጠራ ባለቤት የሆኑት ደቪድ ሲሊቨርማን የተናገሩት።

ከፈጠራ መብት ጥበቃ ጋር በተያያዘ የጥረስ ቀለሙ የያዛቸው ንጥረ ነገሮች ሙሉ በሙሉ ይፋ ያለመሆናቸው ተገልጿል።

ይሁን አንጂ የጥርስ ቀለሙ በረጅም ጊዜ በጥርስም ሆነ በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳደር ስለሚችል የተሰራባቸው ንጥረ ነገሮች ይፋ መደረግ እንዳለባቸው የዘርፉ ባለሙያዎች አስተያየት እየሰጡ መሆኑ ተመላክቷል።

አሁን ላይ የጥርስ ቀለሙ በጠርሙስ እስከ 20 የአሜሪካን ዶላር በቀማሚው ኩባንያ ድረገፅ ላይ እየተሸጠ መሆኑንም ዘገባው ያስረዳል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.