ከመጠን ያለፈ ውፍረት እና ቅጥነት ከእድሜ ላይ 4 ዓመት ይቀንሳል

ከመጠን ያለፈ ውፍረት እና ከመጠን ያለፈ ቅጥነት ከሰዎች የእድሜ ጣራ ላይ በአራት ዓመት እንደሚቀንስ አዲስ የወጣ ጥናት አመልክቷል።

በዓለማችን ላይ በርካታ ሰዎችን አሳትፈዋል ከተባሉ ጥናቶች አንዱ በሆነው እና 2 ሚሊየን ሰዎች በፍቃደኝነት በብሪታንያ ዶክተሮች ተመዝግበው በተሳተፉበት ጥናት ነው ይህ የተባለው።

ተመራማሪዎች በጥናቱ ላይ እንዳስታወቁት አንድ የ40 ዓመት ሰው የቦዲ ማስ ኢንዴክሱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በሚሆንበት ወቅት በበሽታዎች ተይዞ የመሞት እድሉ ይቀንሳል።

ነገር ግን በዚህ እድሜ ሆኖ የቦዲ ማስ ኢንዴክሱ ዝቅተኛ የሆነ ሰው ደግሞ ከጤነኛው ጋር ሲነፃፀር እድሜ የመኖር ሁኔታው ቀንሶ ተስተውሏል ብለዋል።

የአንድ ሰው ቦዲ ማስ ኢንዴክስ የሚለካው አንድ ሰውነት ክብደቱን ከቁመቱ ጋር በማካፈል በሚገኘው ውጤት ነው።

ጤናማ የሚባል ቦዲ ማስ ኢንዴክስም ከ18 ነጥብ 5 እስከ 25 መሆኑንም ነው ተመራማሪዎቹ በጥናታቸው ያመለከቱት።

ታዲያ ይህንን ከልክ ካለፈ ውፍረት እና ቅጥነት ጋር ምን አገናኘው ካላችሁ ጥናቱ ለዚህ መልስ አለው።

ጥናቱ እንዳመለከተው ከልክ ላለፈ የሰውነት ውፍረት የተጋለጡ ወንዶች እና ሴቶች ጤነኛ የወስነት መጠን አላቸው ከተባሉት ጋር የእድሜ ጣራቸው ሲነፃፀር የወንዶች በ4 ነጥብ 2፤ ሴቶች ደግሞ በ3 ነጥብ 5 ቀንሶ ተስተውሏል።

በጣም ቀጭን የሆኑት ላይም የእድሜ ጣራ መቀነስ ተስተውላል የተባለ ሲሆን፤ በዚህም የወንዶች በ4 ነጥብ 3 የሴቶች ደግሞ በ4 ነጥብ 5 ዓመት መቀነሱን ጥናቱ አመላክቷል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

5 Comments

Comments are closed.