ከሲጋራ ሱስ ለማላቀቅ የሚችል ንጥረ ቅመም ማግኘታቸውን ተመራማሪዎች ገለጹ

ከሲጋራ ሱስ ለማላቀቅ የሚችል ንጥረ ቅመም ማግኘታቸውን ተመራማሪዎች ገለጹ።

የካሊፎርኒያ ላ ጆላ ካሊፍ ስክሪፕስ ሪሰረች ኢንስቲቲዩት ተመራማሪዎች ከሲጋራ ሱሰኝነት ለማላቀቅ የሚያስችል ንጥረ ነገር ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

ንጥረ ቅመሙ ለሲጋራ ሱሰኞች በደም ስር የሚሰጥ ሲሆን፥ በሲጋራ ውስጥ የሚገኘው ናይኮቲን የተባለው ሱስ አስያዥ ንጥረ ነገር በደም ውስጥ ለመቀነስ ያስችላል ተብሏል።

ከሱስሽነት ለማላቀቅ እንደሚችል የተነገረለት አዲሱ ንጥረ ቅመም ናይኮቲን የተባለውን ንጥረ ነገር ለአእምሮ ከመድረሱ በፊት በደም ውስጥ ሱስ አስያዥነቱን እንደሚያሳጣው ተገልጿል።

በዚህም ናይኮቲኑ በሱሰኞች ላይ የሚፈጥረውን የሱሰኝነት ስሜት እና ምልክቶች በሂደት በመቀነስ ከሱሰኝነት ለማላቀቅ እንደሚችልም ነው በዘገባው የተገለጸው።

ጥናቱ በእንሰሳት ላይ ተሞክሮ ውጤት ያስገኘ ሲሆን፥ የንጥር ቅመሙን በደም ውስጥ ቆይታ ጊዜ ለማራዘም እና ፈዋሽነቱን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ተጨማሪ ጥናቶች እንደሚደረጉ ተገልጿል።

ተመራማሪዎቹ የዚህን ፈጠራ ውጤት በሰዎች ላይ የመሞከር እቅድ እንዳላቸውም ዘገባው ያስረዳል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.