ተፈጥሯዊ መለያችን ስለሆነው ስለድምጻችን ልናውቃቸው የሚገቡ ሰባት ነጥቦች

ሁሉም ሠው የተለየ ድምጽ ይዞ ነው የሚወለደው።

የቋንቋ አስተማሪ ወይንም ዘፋኝ ሊሆኑ ይችላሉ። ግን ምን ያህል ስለአስደናቂው የሰው ልጅ የተፈጥሮ ሃብት ምን ያህል ያውቃሉ?

የቢቢሲ ሳይንስ ፕሮግራም በዚህ ጉዳይ ላይ ጥናት በማድረግ አስገራሚ ውጤቶችን አግኝቷል።

1. ሁላችንም ከውልደት ጀምሮ የአነጋገር ዘዬ አለን

ህፃንImage copyrightGETTY IMAGES

ህጻናት ማሕጸን ውስጥ እያሉ ጀምሮ ነው የቤተሰቦቻቸውን የአነጋገር ዘዬ የሚይወርሱት።

ተመራማሪዎች አዲስ የተወለዱ ፈረንሳያዊያን እና ጀርመናዊያን ላይ ባደረጉት ምርምር ለቅሷቸው የቤተሰቦቻቸውን ዘዬ የያዘ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ከዚህ በመነሳትም የህጻናትን ለቅሶ ብቻ በመስማት ሃገሮቻቸውን መናገር እንደሚቻል ገልጸዋል።

2. የድምጽ ሳጥናችን ከውስጥ ምን ዓይነት ድምጽ አለው

የድምፅ ሳጥንImage copyrightGETTY IMAGES

ድምጽ የሚጀምረው አየር በተመጠነ መልኩ በድምጽ ሳጥናችን በኩል ከደረታችን ሲወጣ ነው።

ሁለቱ የድምጽ አውታሮች ወይንም ቮካል ኮርዶች አየር ሲወጣ እና ሲገባ ንዝረት የሚፈጥር ሲሆን ይህም ድምጽ ይፈጥራል።

ከዚህ በተጨማሪ እንደ መንጋጋ፣ ምላስ፣ ከንፈር እና ሌሎችም የድምጽ መፍጠሪ አካላችንን በመጠቀም ድምጽ ይፈጠራል።

3. ለምን ይጎረንናል?

በአስራዎቹ የዕድሜ ክልል ያለ ወንድምዎት ሲዘፍን. . .Image copyrightGETTY IMAGES
አጭር የምስል መግለጫበአስራዎቹ የዕድሜ ክልል ያለ ወንድምዎት ሲዘፍን. . .

የወንዶች ድምጽ በጉርምስና ወቅት ይቀየራል። የድምጽ ሳጥናቸው ካለበት ቦታ ትንሽ ዝቅ በማለት ወጣ ለማለት ይሞክራል። ይህም ማንቁርጥ (የአዳም አፕል) በመባል በብዛት ይታወቃል።

በዚህ ምክንያትም በድምጽ ሳጥን እና በአፍ መካከል ያለው ርቀት ይሰፋል።

ርቀቱ መስፋቱ ደግሞ ዝቅ ያለ ድምጽ (ኖት) እንዲኖር እና የወንዶች ድምጽ ጎርናና እንዲሆን ያደርጋል።

ሴቶች በሚያርጡበት ወቅትም አነስተኛ በሆነ ሁኔታ ግን በተመሳሳይ ሂደት ውስጥ ያልፋሉ። ይህም የድምጻቸውን ቅላጼ ዝቅ ያደርገዋል።

4. የሚወዱትን ሠው ድምጽ ያስመስላሉ

ወጣቶች ቤተ-መፅሃፍት ውስጥImage copyrightGETTY IMAGES

አንድን ሠው ስንወድ ድምጻችን ከምንወደው ሠው ድምጽ ጋር እያመሳሰልን እንሄዳሉ።

ለምሳሌ አንዲትን ሴት የወደደ ወንድ ከእሷ ጋር ሲያወራ የድምጹን ቅላጼ ከፍ አድርጎ ነው።

5. እርጅና ሲጫጫን

በእድሜ የገፉ እናትImage copyrightGETTY IMAGES

ዕድሜ ሲጨምር የድምጽ አውታሮች ወይም ቮካል ኮርዶች ስለማይጠነክሩ አየር ማስወጣት ይጀምራሉ። ይህም ድምጻችን የበለጠ ትንፋሽ ያለው ያደርጋል።

በዚህም እድሜአቸው የገፋ ሰዎች የትንፋሽ እጥረት ስለሚያጋጥማቸው ረዣዥም ዓረፍተ ነገሮችን አይናገሩም።

የጡንቻ መድከም ስለሚጨመርበትም ዕድሜ ሲጨምር የድምጻችን ቅላጼ ከፍ ይላል።

6. ድምጻችን ለረዥም ጊዜ ወጣት ሆኖ ይቆያል

ጥሩው ዜና ዕድሜያችን እየጨመረ ሰውነታችን እያረጀ ሲሄድ በድምጻችን ላይ የሚታየው ለውጥ ግን አነስተኛ ነው።

የሠዎችን ድምጽ በመስማት ዕድሜያቸውን ለመገመት ከሞከሩ በአማካይ ዕድሜያቸውን ዝቅ አድርገው ነው የሚገምቱት።

ወጣትImage copyrightGETTY IMAGES

7. ድምጻችንን እንዴት መንከባከብ እንችላለን?

ዕድሜያችን ሲጨምር እንደሠውነታችን ሁሉ የድምጻችን ጡንቻዎችም ተከታታይ ልምምድ ይፈልጋሉ።

ይህን የድምጽ ልምምድ በማድረግ የድምጽ አውታሮችን በመለጠጥ በጥሩ ደረጃ ላይ ሊያቆዩ ይችላሉ። (ግን ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ አይደለም የሚለማመዱት)

  • እንደ ‘ሃና’ የመሳሰሉ ድምጾችን በመምረጥ በሚችሉት መጠን ይለጥጡት። ረዘም አድርገው ድምጽዎን በማጉላት ይለማመዱ።
  • ሲጀምሩ ከፍ አድርገው ይጀምሩ፡ ሃሃሃሃሃ-ሃ-ሃ ሃ ሃ ሃ. . .
  • ድምጽዎ እወረደ እስኪሄድ ድረስ ይቆዩ: ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ. . .
  • ዝቅ ብለው እስከሚችሉት ድረስ ለመቀጠል ይሞክሩ: ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ-ና-ና-ና
  • ቃሉ መጨረሻ ላይ ስንደርስ የሚሰባበረው አየር ሲያጥረን ነው።
  • ይህንኑ ይድገሙ

ወይንም ደግሞ የዘፈን ቡድን ውስጥ መግባትም ሌላኛው አማራጭ ነው። ይህም ድምጻችን ጤነኛ እንዲሆን ከመርዳቱም በላይ በመዝፈናችን እና ከሌሎች ጋር በመተዋወቃችን የሚያዝናናን ይሆናል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

10 Comments

Comments are closed.