NEWS: አንጋፋዋ አርቲስት ዓለምፀሀይ ወዳጆ ወደ ሀገሯ ተመለሰች፡፡

አርቲስት ዓለምፀሀይ ወዳጆ ከኢትዮጵያ ከወጣች 27 ዓመታት በኋላ ዛሬ አዲስ አበባ ገብታለች፡፡

አርቲስት ዓለምፀሀይ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማሪያም ከሀገር በወጡ በቀናት ልዩነት ነበር ለስደት የተዳረገችው፡፡

አርቲስቷ በምትኖርበት አሜሪካ በርካታ የጥበብ ስራዎችን ለታዳሚያን ስታደርስ ቆይታለች፡፡
ዓለምፀሀይ ወዳጆ ጤና ለጣና በተሰኘው ጣናን ከእንቦጭ የመታደግ ስራ በመሳተፍ ለጣና በርካታ አስተዋጽኦ ያበረከተች አርቲስት ናት፡፡
አበበ በለው ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

ዓለምፀሀይ ወዳጆንና አበበ በለውን ዛሬ አዲስ አበባ ሲደርሱ በቦሌዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በርካታ የጥበብ ሰዎች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ምንጭ: Amhara Mass Media Agency

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.