‹‹ባለፉት ዓመታት አማራ እና ኦሮሚያን ለመከፋፈል እሳት እና ጭድ ያቀበሉን ሙተንም ቢሆን አሁን የምንፈልገው ኢትዮጵያዊነት ላይ ደርሰናል።›› ጀዋር ሙሀመድ

ዘጋቢ፡-ግርማ ተጫነ

የኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ እና አክቲቪስት ጀዋር ሙሃመድ በባሕር ዳር አቫንቲ ብሉ ናይል ሆቴል ተገኝቶ ከወጣቶችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

• በራሳችን መፋቀድ በዚህ ፍጥነት ተቀራርበን በመስራታችን መሰረት ለሆኑ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ታላቅ ምስጋና አለኝ።
• ለውጡን እውን ለማድረግ ተቀራርበን መስራት ይስፈልጋል። ለዚህም ነው ለለውጡ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከከፈሉ ህዝቦች ጋር ለመወያየት የመጣሁት ።
• ባለፉት ዓመታት አማራ እና ኦሮሚያን ለመከፋፈል እሳት እና ጭድ ያቀበሉን ሙተንም ቢሆን አሁን የምንፈልገው ኢትዮጵያዊነት ላይ ደርሰናል።
• የሁለቱ ህዝቦች መቀራረብ እንደ አባት እና ልጅ ነው። ምሁራን እና አክቲቭስቶች ህዝቡን ለማቀራረብ መስራት የሚያስፍገን ጊዜ ነው።
የኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ እና አክቲቪስት ጀዋሪ ሙሃመድ በብሉ ናይል ሆቴል ውይይቱ ተሳታፊዎች ጥያቄ ማቅረብ ጀምረዋል።

ምንጭ:  Amhara Mass Media Agency

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.