አዲሱ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አህመድ አብዲ ማን ናቸው?

የቀድሞውን የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሐመድ ኦማርን የተኩት አህመድ አብዲ ሼክ ሞሃመድ (ኤልካስ) በፊቅ ዞን ገርቦ በተባለ ስፍራ ተወለዱ ።

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ከተማ በጊዜው በልማት ወደኋላ ለቀሩ ታዳጊ ክልሎች አገልጋሎት እንዲሰጥ በተቋቋመው ዕድገት አዳሪ ትምህርት ቤት ተምረዋል።

በ2001 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኋላ፤ ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በ2004 ዓ.ም በቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ትምህርት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀዋል።

ከምረቃ በኋላ በሶማሌ ክልል ጎዴ እና ጂግጂጋ ከተሞች የገቢዎች መስሪያ ቤት ባልደረባ ሆነው በመስራት የሥራ ዓለምን ተቀላቅለዋል ።

“አብዲ ሞሃመድ ኡመር ስልጣን ለመልቀቅ በተደጋጋሚ ጠይቀው ነበር” አዲሱ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት

አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ዋሉ

በጅግጅጋ ግጭት ሸሽተው የተሸሸጉ ሰዎች በከፋ ችግር ላይ ናቸው ተባለ

በ2006 ዓ.ም የቀብሪ ደሃር ከተማ ከንቲባ ሆነው የተሾሙ ሲሆን በቀጣይ ዓመት ደግሞ የክልሉ ምክትል የፋይናንስ ሃላፊ ሆነው ለመስራት ችለዋል።

ከ2008 ዓም ጀምሮ የክልሉ የፋይናንስ ቢሮ ዋና ሃላፊነትን ተረክበው የሰሩ ሲሆን ከሦስት ወራት ወዲህ የክልሉ የውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ሃላፊ ሆነው እየሰሩ ነበር።

በ2009 ዓ.ም ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በ’ዲዛስተር ማኔጂመንት’ ተመርቀዋል።

በ30ዎቹ ዕድሜ መጀመሪያ የሚገኙት አቶ አህመድ ሼክ ሞሐመድ ባለትዳር እና የሰባት ልጆች አባት ናቸው።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement