Beloved Artist Fekadu T/Mariam Passed Away | አርቲስት ፍቃዱ ተክለማሪያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አርቲስት ፍቃዱ ተክለማሪያም በትላንትናው ዕለት ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡

ፍቃዱ አብዛኛውን የዕድሜውን ክፍል በመድረክ ያሳለፈ ሲሆን በርካታ ቲያትሮችንም ተጫውቷል፡፡

እንዲሁም በሬዲዮ ድራማዎች፣ በመጽሐፍት ትረካዎች፣ በቴሌሺዥን ድራማዎች ላይ እንዲሁ በርካታ ፊልሞች ላይ ተሳትፏል፡፡

በጥቅሉ ፍቃዱ በመድረክ ላይ ከ33 ዓመታት በላይ አሳልፏል፡፡

በዚህ ጊዜ ውስጥ ታዲያ ከተጫወተባቸው ተውኔቶች መካከል ኦቴሎ፣ ኤዲፐስ ንጉሥ፣ ሐምሌት፣ ቴዎድሮስ፣ ንጉሥ አርማህ፣ መቃብር ቆፋሪውና የሬሣ ሳጥን ሻጩ፣ የሰርጉ ዋዜማ፣ አቡጊዳ ቀይሶ፣ ባለካባ ባለዳባ፣ መልዕክተ ወዛደር እና ሌሎችም ታዋቂነትን ያተረፉለት ተውኔቶችን በብቃት ተውኗል፡፡

 

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.