NEWS: የኤምሬትስና የአፍሪካ ቀንድ የገንዘብ ፖለቲካ?

ትናንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መዲና አቡዳቢ ተገናኝተዋል።

መሪዎቹ ከአልጋ ወራሹ ልዑል ሼክ መሃመድ ቢን ዘይድ ጋር በሁለትዮሽ ስምምነቶችና በቀጠናው ጉዳይ መወያየታቸውን እንዲሁም የሁለቱ ሃገራት መሪዎች በመካከላቸው ሰላም እንዲወርድ በማድረጋቸው ልዑሉ የሃገራቸውን ከፍተኛ ሜዳልያ እንደሰጧቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

ኢትዮጵያ በዱቤ ተጨማሪ ነዳጅ ከሳኡዲ አረቢያ ጠየቀች

“ኢህአዴግ ተዳክሟል ብላችሁ እንዳትሳሳቱ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በጉዞ በተጨናነቀው አጭር የስልጣን ዘመናቸው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን ሁለት ጊዜ እንዲሁም ሳዑዲ አረብያን መጎብኘታቸው ይታወሳል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጉብኝት ተከትሎ የተባበሩት ኤምሬትስ በቀጥታ ወደ ማእከላዊ ባንክ የሚገባ እንዲሁም በውጭ የቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መልክ ለኢትዮጵያ በጥቅሉ 3 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት መስማማቷም ይታወቃል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በአጠቃላይ የባህረ ሰላጤው አገራት ከአፍሪካ ቀንድ አገራት ጋር ግንኙነታቸውን እያጣደፉ መሆኑ ምን ያሳያል? በአካባቢው ፖለቲካ ላይስ ምን አይነት ተፅእኖ ያሳድራል?

ዶላር በጥቁር ገበያ ለምን ቀነሰ?

የዲያስፖራው አንድ ዶላር

የባህረ ሰላጤው አገራት ፍላጎት ለምን ናረ?

በመልክአ ምድር ሲታይ የአፍሪካ ቀንድ ለመካከለኛው ምሥራቅ እጅግ ቅርብ የሚባል ነው። ይህ ሁኔታ አካባቢውን ቁልፍ ቦታ አድርጎታል።

ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የባህረ ሰላጤው የአፍሪካ ቀንድ ቅርምት ፍላጎት እየጋመ መጥቷል። ለምን?

በኬል ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር የሆኑት ዶ/ር አወል አሎ ሁለት አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ምክንያቶችን ያነሳሉ።

በኢራን የሚመራው የሺዓ ሃይማኖታዊ ቀኖና ቡድን እና በሳኡዲ ከሚመራው የሱኒ ጥምረት ጋር ያለው ፖለቲካዊ ልዩነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ መጥቷል። የዚህ ልዩነት ነጸብራቅ የመን ላይ እየተካሄደ ያለው የውክልና ጦርነት በይበልጥ ይገልጸዋል።

እነ ሳኡዲ ኤርትራና ጅቡቲ ወርደው ወደቦችን ሲያለሙ ለሸቀጥ ማራገፊያ ብቻ እንዳልሆነ የሚናገሩት ዶ/ር አወል” አንድ አገር የሌላ አገር ሄዶ ወደብ ሲያለማራ ትልቅ ኢንቨስትመንት ነው። በዚህ አካባቢ ደግሞ የወደብ ልማቶቹ የኮኖሚያዊ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ እንድምታ አላቸው።

ታዲያ እነዚህ በበርካታ ሪያል ወደብ የተሠራላቸው አገሮች ውለታ ሲጠየቁ እምቢ የሚሉበት እድል እምብዛምም ነው። “ይላሉ

ከፖለቲካ አንጻር ጫና ውስጥ እንደሚከታቸው ዶ/ር አወል ይናገራሉ።

ከዚህም ባሻገር ጦርነቱ አድማሱ እየሰፋ መምጣቱና የአካባቢው ፖለቲካ እየተቀየረ መሆኑ የባህረ ሰላጤው የአፍሪካ ቀንድን ቸል እንዲሉት አልሆነም።

የዶክተር ዐብይ አሕመድ ‘ፑሽ አፕ’

የሪያል ፖለቲካ

ዶ/ር አወል አሎ በአፍሪካ ቀንድና በባህረ ሰላጤው አገሮች ያለውን ግንኙነት ጥቅል ባሕሪያቸውን በመግለጽ ይጀምራሉ።

አብዛኛው የባህረ ሰላጤው አገሮች ሊሰጡ የሚችሉትና አፍሪካ አገሮች የሌላቸው ጥሬ ገንዘብ ነው። ለነ ሶማሊያ ለነ ኤርትራ ቀጥተኛ የሆነ የበጀት ድጎማ እስከማድረግ የደረሱትም ለዚሁ ነው።

በምላሹ ታዲያ የባህረ ሰላጤው አገሮች ፍጹማዊ የፖለቲካ ታማኝነት መጠበቃቸው አልቀረም። ለዚህም ነው ግንኙነቱ “የሪያል ፖለቲካ” የሚለውን ስያሜ የያዘው።

” የባህረ ሰላጤው ፖለቲካ ትራንስአክሽናል ነው” የሚሉት አቶ አወሎ ግንኙነቱ ከዲፕሎማሲ ይልቅ ይሄን አድርጌልኻለሁና ያንን አድርግልኝ በሚል የገንዘብ ውለታ መቀፍደዱ የራሱ አሉታዊ ጎን እንደሚኖረው አልሸሸጉም።

የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ከዚህ ግንኙነት ምን ያተርፋሉ? ምን ያጣሉ የሚለው ጥያቄም የሚመለሰው በዚሁ የግንኙነት መርህ ነው።

ሁለቱም ወገኖች አገራዊ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ዘላቂ ግንኙነትን ካስቀደሙ ሁለቱም ወገኖች ይጠቀማሉ።

ነገር ግን የአፍሪካ ቀንድ አገራት ፖለቲካዊ ተቋማት ያለባቸው ድክመት ሲታይና የባህረ ሰላጤ አገራት ላይ ያለው የፖለቲካ ባህል ሲታይ የሕዝቦቻቸውን ጥቅም የሚያስጠብቅ ግንኙነት ላይሆን እንደሚችል ምሁሩ ይገምታሉ።

ያም ኾኖ ግንኙነቱ አሉታዊ ነው ብለው አይደመድሙም። “አዲስ ግንኙነት (ኢንጌጅመነት) ነው፤ ገና ጊዜ ወስዶ ማየት ያስፈልጋል።” ይላሉ።

የተባበሩት ኤምሬትስ አዲስ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ?

በለንደን የሚገኙት ኤርትራዊው የፖለቲካ ተንታኝ አቶ አብዱራህማን ሰኢድ ከባህረ ሰላጤው አገራት አንዷ የሆነችው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ካለፉት ጥቂት ጊዜአት ወዲህ አዲስ የውጭ ሃገር ፖሊሲ እየተከተለች መሆኗንና በዚህም ባለችበት አካባቢ ከፖለቲካ ገለልተኝነት ወደ ፖለቲካዊ ተሳትፎ እየመጣች መሆኑን በቀዳሚነት ይጠቅሳሉ።

ቀጥለውም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አገራት ከሳኡዲ አረብያ ጋር በመሆን የመን ውስጥ እያካሄዱት ያውን ጦርነት፣ ኤምሬቶቹ እንደ ኤርትራ ባሉ የአፍሪካ ቀንድ አገራት የባህር ሃይል ጣቢያ መገንባትን በማሳያነት ያነሳሉ።

እሳቸው እንደሚሉት የእነዚህ የባህረ ሰላጤው ቡድን አገራት በሌላኛው ወገን ካለው ኢራንና ኳታር ምድብ አገራት ጋር ከፍተኛ እሰጥ አገባና የፖለቲካ ተፅእኖ መገፋፋት ላይ መሆናቸው ወሳኝ ሁነት ነው።

“ከእነዚህ አገራት ጋር የሚፈጠር ወታደራዊ መፍጠሩ አደጋ ይኖረዋል።አደጋው እነዚህ አገራት ወደ ጦርነት ሲገቡ የአፍሪካ ቀንድ አገራትም በተዘዋዋሪ ጦርነቱ ውስጥ መግባታቸው ነው” በማለት ወታደርም ባትልክ በየመን ጦርነት የኤርትራ እጅ አዙር ተሳትፎን በምሳሌነት ይጠቅሳሉ።

ይህን የባህረ ሰላጤው አገራት የፖለቲካ ፍትጊያ ታሳቢ በማድረግ ለአፍሪካ ቀንድ አገራት ኤርትራ ፣ ኢትዮጵያ ፣ ሶማሊያና ጅቡቲም ሆነ ኬንያና ሱዳን ከአገራቱ ጋር የሚደረግ ጥብቅ ግንኙነት ጊዜያዊ እንጂ ዘለቄታዊ ጥቅም እንደሌለው ይደመድማሉ።

የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት የግንኙነቱን አደጋ በመቀነስ ተጠቃሚነታቸውን ሊያረጋግጡ የሚችሉበት መንገድ ለሳቸው አንድና አንድ ነው።

አገራቱ በተናጠል ሳይሆን እንደ ምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት ኢጋድ አባልነት አንድ ላይ በመቆም ከባህረ ሰላጤው አገራት ሊመጣባቸው የሚችለውን ተፅእኖ ሊገቱት እንደሚችሉ ያምናሉ።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.