ሶማሊያዊ አባት የአስር ዓመት ልጁን በግርዛት ሳቢያ በሞት ቢነጠቅም ግርዛትን ከማሞገስ አላገደውም

የአስር ዓመት ልጁ በግርዛት ሳቢያ የሞተችበት ሶማሊያዊ አባት “ባህላችን ነው” ሲል ግርዛትን አወድሷል።

ዳሂር ኑር የተባለው ግለሰብ ልጅ የሶማሊያ ባህላዊ ገራዦች ዘንድ ለግርዛት ከተወሰደች በኃላ ለሁለት ቀናት ደሟ ያለማቋረጥ ፈሶ በስተመጨረሻ ህይወቷ አልፏል።

አባትየው በበኩሉ ልጁን የነጠቀውን የግርዛት ባህል ሳይኮንን “የአካባቢው ነዋሪዎች ባህል ነው” በማለት ለቪኦኤ ተናግሯል።

የታዳጊዋን ህይወት ለማትረፍ ከተረባረቡ የህክምና ባለሙያዎች አንዱ ዶ/ር አብዱራህማንኦማር ሀሰን “በዚህ ሁኔታ የተገረዘ ሰው በህይወቴ ገጥሞኝ አያውቅም” ብለዋል።

ኢትዮጵያ በዱቤ ተጨማሪ ነዳጅ ከሳኡዲ አረቢያ ጠየቀች

”ኤርትራ የእምነት ነፃነት የምታከብር ሃገር ነች” አቶ የማነ ገብረ-መስቀል

የ “ጥርስ አልባው” ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ?

በዱሳማረብ ከተማ የሚገነው ሀናኖ ሆስፒታል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አብዱራህማን ታዳጊዋን ለመግረዝ ጥቅም ላይ የዋሉ ስለቶች ንጹህ እንዳልነበሩ አክለዋል።

የታዳጊዋ አባት ግን ለልጃቸው ሞት ማንንም ተጠያቂ እንደማያደርጉ ተናግረዋል።

ጋሌኮ ኤዱኬሽን ሴንተር ፎር ፒስ ኤንድ ዴቨሎፕመንት የተሰኘው የመብት ተከራካሪ ቡድን ዳይሬክተር ሀዋ አደን መሀመድ አባትየው ክስ ቢከፍትም ትርጉም አልባ መሆኑን ይናገራሉ።

“ልጅቷን የገረዟት ሴት በቁጥጥር ስር አልዋሉም። ቢታሰሩም የሚቀጣቸው ህግ የለም” ብለዋል።

ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች

ኤርትራ የሃይማኖት እሥረኞችን ፈታች

ጉዳዩ ዘወትር ሶማልያ ውስጥ ከሚስተዋሉ የግርዛት ጉዳዮች እንደማይለይም ተናግረዋል።

በሀገሪቱ በግርዛት ሳቢያ የሴት መራቢያ አካል ውጫዊ ክፍል ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ይወገዳል። ሴቶች አስከፊ የጤና እክልም ይገጥማቸዋል።

በሶማሊያ ህገ መንግስት ግርዛት ክልክል ቢሆንም 98 በመቶ የሀገሪቱ ሴቶች እንደሚገረዙ የዩኒሴፍ መረጃ ያሳያል።

ሶማልያ ውስጥ ግርዛትን እንደ ሀይማኖታዊ ግዴታ የሚያዩ በርካቶች ናቸው። ፖለቲከኞች እነዚህን የማህበረሰቡ አካላት ላለማስቀየም ግርዛትን ለማስቀረት መመሞከርን አይደፍሩም።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.