የሰረቀውን ወርቅ ከይቅርታ ደብዳቤ ጋር የመለሰው ሌባ

ከመኖሪያ ቤት በርከት ያሉ ወርቆችን የሰረቀው ግለሰብ ከሁለት ቀናት በኋላ ከይቅርታ ደብዳቤ ጋር ወርቁን መመለሱ ተሰምቷል።
ነገሩ የሆነው በደቡብ ህንድ በምትገኘው ከራላ ግዛት አምብላፕሁዛ ከተማ ውስጥ ነው።

ሌባው ወደ መኖሪያ ቤቱ ሰብሮ ሊገባ የቻለው የቤቱ ባለቤቶቹ የዘመድ ሰርግ ላይ ለመታደም ሀገር ሰላም ብለው ቤታቸውን ቆልፈው በወጡበት ወቅት ነበር።

ሌባውም በጓሮ በኩል በር ሰብሮ በመግባት የጣት ቀለበት እና የጆሮ ጌጥን ጨምሮ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ያገኛቸውን የወርቅ ጌጣ ጌጦች ሰርቆ ይሰወራል።

ባለቤቶቹም ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲመለሱ ቤታቸው መዘረፉን ይረዱና ወዲያው ለፖሊስ ያመለክታሉ።

ታዲያ ከሁለት ቀናት በኋላ የጠፋባቸው የወርቅ ጌጣ ጌጥ እና የይቅርታ ደብዳቤ ቤታቸው ድረስ የመጣላቸው ቤተሰቦቹ፤ በተፈጠረው ነገር መገረማቸውንም ይናገራሉ።

ግለሰቡ በላከላቸው የይቅርታ ደብዳቤ ላይም “እባካችሁ አታሳስሩኝ፤ እንደዚህ አይነት ስህተት የሰራውን ያለሁበት አስቸጋሪ ሁኔታ አስገድዶኝ ነው” ብሏል።

ፖሊስ በበኩሉ ግለሰቡ ወርቁን መመለሱን ተከትሎ በእሱ ላይ የተከፈተ ክስ እንደሌለ ነው ያስታወቀው።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.