NEWS: Fire Broke Out At The Great Anwar Mosque | ታላቁ አንዋር መስጊድ ቃጠሎ ደረሰበት፡፡

ዛሬ ከሌሊቱ 9 ፡30 ገደማ የእሳት አደጋ ቃጠሎው እንደተቀሰቀሰ የገለፁት የአይን እማኞች በመስጊዱ ዙሪያ ባሉ ሱቆችና መጋዘኖች ላይ ውድመት አስከትሏል፡፡
ከተወሰነው የሴቶች መማሪያ ክፍል በስተቀር ዋናው መስጊድ ከቃጠሎው መትረፉ ተገልጿል፡፡
እሳቱን ለማጥፋት የአካባቢው ማህበረሰብና የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን ሰራተኞች ተረባርበዋል፡፡
ቃጠሎው ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉም ተነግሯል፡፡
የእሳት አደጋው መንስኤና የደረሰው የጉዳት መጠን እስካሁን አለመታወቁን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊን ስለአደጋው ማብራሪያ ለመጠየቅ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ምንጭ: ኢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.