Nura Hussien; The Woman Who Killed Her Abusive Husband | ባሏን በስለት የገደለችው ኑራ ሁሴን

የሱዳን ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የኑራ ሁሴንን የሞት ፍርድ ቀልብሶታል። ኑራ አስገድዶ የደፈራትን ባለቤቷን በመግደሏ የሞት ፍርደኛ ነበረች።

የ19 ዓመቷ ኑራ አሁን በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት ብቻ እንድትቀጣ ተወስኖላታል።

እናቷ ዘይነብ አሕመድ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ልጃቸው ኑራ ሕይወቷ በመትረፉ እጅግ ደስተኛ ሆናለች።

በዓለም ታዋቂና ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ ሰዎች “ፍትህ ለኑራ” የሚል የማኀበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ከፍተውላት ነበር።

ባለፈው ወር ኢስላማዊው ፍርድ ቤት ኑራ በስቅላት እንደትቀጣ ወስኖባት ነበር።

ኑራ ሁሴን ባለቤቷ የአክስት ልጆቹን ሰብስቦ እጅና እግሯን ጠፍረው እንዲይዙለት ካደረገ በኋላ ይደፍራት እንደነበርና ይህንኑ ተግባሩን ለሁለተኛ ጊዜ ለመፈጸም ሲሞክር ግን በቢላ በመውጋት እንደገደለችው ተዘግቧል።

ኑራ ወደዚህ ትዳር የገባችው በ16 ዓመቷ ተገዳ ሲሆን ባለቤቷ የአክስቷ ልጅ ጭምር ነው። የ16 ዓመት ታላቋ ቢሆንም።

የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት ፈንድ እንደሚለው በሱዳን ከሦስት ሴቶች አንዷ ዕድሜዋ ከ18 በታች ሳለ ትዳር ትምሰርታለች።

የኑራ እናት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ልጃቸው በገዛ ባለቤቷ ከተደፈረች በኋላ ራሷን ጠልታ ነበር። ቢላዋውንም ያዘጋጀችው የራሷን ሕይወት ለማጥፋት ነበር።

ድርጊቱን ከፈጸመች በኋላም ወደ ቤተሰቧ በመሄድ የሆነውን ሁሉ ነግራቸዋለች። አባቷም የበቀል እርምጃን በመስጋት መላ ቤተሰቡን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይዘው መሄዳቸው ተዘግቦ ነበረ።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.