NEWS: “ለኤርትራ ልዑክ ቡድን አቀባበል እናደርጋለን” አቶ መለስ አለም

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ልዪ ልዑክ ቡድን ወደ አዲስ አበባ እልካለሁ ማለታችውን ኢትዮጵያ በጥሩ መልኩ እንደምታየው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል-አቀባይ አቶ መለስ አለም ገልፀዋል።

“ይህንን ጉዳይ የኢትዮጵያ መንግሥትረ በበጎ ይመለከታዋል፤ በብዙ ወገኖች ዘንድ እንደመልካም ምስራችም ዜና ተወስዷል።” ብለዋል መለስ አለም

ከዚህም በተጨማሪ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት፣ኢጋድና እንዲሁም መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ድርጅቶች ድጋፋችውን እያደረጉ መሆናቸውን ገልፀው ፋይዳው ለቀጠናው ከፍተኛ እንደሆነም ገልፀዋል።

“በኢትዮጵያና በኤርትራ መሀከል የሚኖር ሰላም ከሁለቱ ኃገራት ባለፈ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት በጣም ጠቃሚ እንደሆነ ፋይዳው ከክልሉ በላይም እንደሆነ መግለጫ ሰጥተዋል።” ያሉት አቶ መለስ አለም

በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ለኤርትራ ልዑካን አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት እንደሚኖር ተናግረዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ አገራት የሚገኙ አምባሳደሮች በፖለቲካ ባላቸው አቋም የተነሳ ወደ ሀገር ውስጥ ተጠርተው እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ መለስ አለም ሲመልሱ

“በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአምባሰደሮች መጠራት አዲስ ነገር አይደለም። የመደበኛ ሥራው አካል አድርጎ መውሰድ ያስፈልጋል። ከዚያ ውጭ ግን የተጠቀሱትን አምባሳደሮች ተጠርተዋል ስለተባለው የወጣው ዘገባ ትክክለኛነት ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነው።” ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የደቡብ ሱዳን ግጭት መፍታትን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሁለቱን ተፎካካሪዎች ለማስማማት የተደረገው ሙከራ የተሳካም እንደሆነ ገልፀዋል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.