NEWS: We Can Denuclearize Only When We Are Considered As Friend Not Enemy | ኒውክሌርን ማስወገድ የምንችለው በጠላትነት መተያየት ስናቆም ብቻ ነው – ኪም

በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጁንግ ኡን በዋሽንግተን እና ፒዮንግያንግ መካከል በጠላትነት መንፈስ መተያየት መቆም ከቻለ ብቻ ነው ልሳነ ምድሩ ከኒውክሌር ነጻ መሆን የሚችለው ብለዋል፡፡

የሀገሪቷ መገናኛ ብዙኀን እንደዘገቡት ከሆነ ትላንት በሁለቱ መሪዎች መካከል የተካሄደው ውይይት እርስበርስ የሚያደርጉት ወታደራዊ እሰጣ ገባ እና ፀብአጫሪነት ማቆም እንዳለባቸው መመካከራቸውን አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም ዩናይትድ ስቴትስ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ነሃሴ ላይ የምታደርገውን ወታደራዊ ልምምድ ለማቆም መስማማቷም በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

ሁለቱ መሪዎች እርስበርስ የጉብኝት ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፥ ትራምፕ ፒዮንግያንግን ኪም ደግሞ ዋሽንግተንን ለመጎብኘት እሽታቸውን ገልጸዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ከደቡብ ኮሪያ ጋር የምታደርገውን ወታደራዊ ልምምድ ለማቆም መወሰኗን ተከትሎ የአካባቢው ሀገራት ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

ደቡብ ኮሪያውያን በበኩላቸው ታራምፕ ወታደራዊ ልምምዱን ለማቆም መስማማታቸውን አልወደዱትም ተብሏል፡፡

የጃፓኑ የመከላከያ ሚኒስትር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወታደራዊ ልምምዱ ለሰሜን እሲያ ሀገራት ጸጥታ አስፈላጊ መሆኑን አንስተው መቋረጥ የለበትም ብለዋል፡፡

እስከአሁን ድረስ ሁለቱ መሪዎች ያደረጉት ዝርዝር ስምምነት ይፋ ያለመሆኑን ተከትሎ ምናልባትም ይህ የሆነው ሀገራቱ በተመሳሳይ አቋም ላይ ስለማይገኙ ይሆናል እያሉ ነው የፖለቲካ ተንታኞች፡፡

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.