NEWS: የሰሜን ኮርያዉ ፕሬዝዳንት ኪም ሲንጋፖር ደርሰዋል፡፡

በእያዩ መለሰ

የሰሜን ኮርያዉ ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን ከአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለሚያደርጉት ቀን የተቆረጠለት ስብሰባ ነዉ ሢንጋፖር የገቡት፡፡

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ታሪካዊ ስብሰባ በመጭዉ ማክሰኞ ሴንቶሳ በተባለች ደሴት ይካሄዳል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ በዛሬዉ እለት ዘግየት ብለዉ ሲንጋፖር እንደሚደርሱ እየተጠበቀ ነዉ፡፡
ዋሺንግተን ስብሰባዉ በመጨረሻ ኪም የኒዉከለር መሳሪያዎቻቸዉን ለማስረከብ ሂደቱ የማስነሻ ቁልፉን የሚጫኑበት ነዉ ስትል ተስፋ አድርጋለች፡፡

በተለይም ባለፉት አስራ ስምንት ወራት ዉስጥ ሁለቱ መሪዎች የማይጨበጥ ግንኙነት የነበራቸዉ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከመዘላለፍ እና ጠባ አጫሪነት በተለየ ፊት ለፊት ሊገናኙ ነዉ፡፡

ትራምፕ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደገለፁት በሀገራቱ መካከል ያለዉን መሰረታዊ ችግር ለመፍታት አስተማማኝ እድል አለ ብለዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች ከስብሰባችዉ ቀደም ብለዉ ከሲነጋፖሩ ጠቅላይ ሚኒስተር ሊ ሀሲን ሉንግ ጋር ይገናኛሉ ተብሎል ይጠበቃል፡፡

ምንጭ:  Amhara Mass Media Agency

 

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.