ማንኮራፋትን የምንከላከልባቸው መንገዶች

ማንኮራፋት የምንለው በምንተኛበት ጊዜ በመተንፈሻ አካላችን ላይ በሚፈጠሩ ለውጦች ምክንያት በሚመጣ ድምፅ ነው። ማንኮራፋት አብሮ የሚተኛን ሰው ከመረበሽ ባለፈ አንዳንድ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የጤና እክሎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
► ለማንኮራፋት ተጋላጭነት የሚዳርጉ ሁኔታዎች
የሰውንት ክብደት መጨመር:­ በተፈጥሮ የሚኖር ጠባብ መተንፈሻ አየር የምናስገባበት አካል መጥበብ የምንስበው አየር ግፊት እንዲጨምር በማድረግ ድምፅን ይፈጥራል 
አልኮል መጠጥ ማብዛት፡­ የአልኮል መጠጥ የጉሮሮ ጡንቻዎችን በማፍታታት አየር በሚገባበት ወቅት ርግብግቢት በመፍጠር ድምፅ እንዲጨመር ያደርጋል
በአፍንጫ ላይ የሚከሰቱ ችግሮች፡­ በአፍንጫ ላይ የሚኖሩ ተፈጥሮአዊ የአቀማመጥ ችግሮች የማንኮራፋት ዕድልን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራሉ
► ማናኮራፋት የሚያስከትላቸው ችግሮች
ቀን ቀን የእንቅልፍ ስሜት መሰማት ብስጭትና ንዴት
ለነገሮች ትኩረት ማጣት ለደም ግፊትና ለልብ ሕመም ማጋለጥ
በእንቅልፍ እጦት ምክንያት ለሰው ሠራሽ አደጋዎች መጋለጥ
የትዳር አጋርን እንቅልፍ ማሳጣት ናቸው፡፡
► የሚያንኮራፉ ሰዎች
በእንቅልፍ ጊዜ የሚረብሽ ድምፅ ያሰማሉ የቀን እንቅልፍ ሊያስቸግራቸው ይችላል የጉሮሮ መከርከር ይኖርባቸዋል ሰላም የሌለው እንቅልፍ ያስቸግራቸዋል በእንቅልፍ ጊዜ ትንታ እና ትንፋሽ ማጠር ያጠቃቸዋል የደረት መጨምደድና የደም ግፊት ሊኖራቸው ይችላል፡፡
► ማንኮራፋትን የምንከላከልባቸው መንገዶች
አስተኛኘትዎን ያስተካክሉ በጀርባዎ መተኛት ላንቃዎን ወደ ጉሮሮ እንዲወርዱ ስለሚያደርግ በእንቅልፍ ጊዜ የመርገብገብ ድምፅን እንድናሰማ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ በጎን መተኛት መፍትሔ ሊሆን ይችላል፡፡
የሰውነት ክብደትዎን ይቀንሱ የሰውነት ክብደት የሌላቸው ሰዎችም ቢሆኑ ያንኮራፋሉ፡፡ ነገር ግን ማንኮራፋቱ የመጣው የሰውንት ክብደት ከጨመረ በኋላ ከሆነ መንስዔው ሊሆን ስለሚችል ክብደትዎን ይቀንሱ፡፡
የአልኮል መጠጥ አይውሰዱ የአልኮል መጠጥ የምንወስድ ከሆነ በጉሮሮ አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎችን ስለምናፍታታ ማንኮራፋት እንጀምራለን፡፡
ከመተኛታችን በፊት ባለው ከ4 – 5 ሰዓት ጊዜ ውስጥ አልኮል መጠጥን መውሰድ ማናኮራፋትን ያባብሳል፡፡ የእንቅልፍ ሰዓትዎን ያስተካክሉ ለረጅም ሰዓታት ያለዕረፍት የሚሠሩ ከሆነ እና በመጨረሻ እጅግ በጣም እራስዎን ካዳከሙ በኋላ የሚተኙ ከሆነ የጉሮሮ ጡንቻዎች ባጣም ስለሚፈታቱ የማንኮራፋት ድምፅ ያሰማሉ፡፡

አፍንጫዎን ከመደፈን ይከላከሉ አፍንጫዎ በቅዝቃዜም ሆነ በአለርጂ ምክንያት ከተደፈነ የማንኮራፋት ዕድልን ሰለሚጨምር ከመተኛትዎ በፊት በሙቅ ውሃ ገላን መታጠብ በተጨማሪ ውሃ በጨው በማድረግ አፍንጫን ማፅዳት፡፡ ይህ የአፍንጫን ቀዳዳዎች ስለሚከፍት ማንኮራፋትን ይከላከላል፡፡ ትራሰዎን ይቀይሩ በትራስዎ ውስጥ በዓይን የማይታዩ ብናኞች ተከማችተው ሊገኙ ስለሚችሉ መቀየር ተገቢ ነው፡፡ ፈሳሽ በብዛት ይውሰዱ ፈሳሽን በብዛት መውሰድ ከአፍንጫችን የሚመነጨውን ፈሳሽ ሰለሚያቀጥን ማነኮራፋት እንዳይኖር ይረዳል፡፡

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.