“ትራምፕ ጤነኛ ናቸው አልወጣኝም” ሲል የቀድሞው የግል ሐኪማቼው ተናገረ

በአውሮፓውያኑ 2015 ዶናልድ ገና ዕጩ ሳሉ የግል ሐኪማቸው ናቸው የተባሉ ሰው “ትራምፕ እጅጉን ጤናማ ፍጡር ከመሆናቸው የተነሳ እስካዛሬ ከነበሩ የአሜሪካ መሪዎች ሁሉ በፍጹም መልካም ጤንነት ላይ የሚገኙት መሪይ ሆናሉ” ሲሉ ተናገረው ነበር።

ለጥቆም ኒውዮርክ ታይምስ የተሰኘው ጋዜጣ እኒህን ሐኪም ጠቅሶ እንደዘገበው ዶናልድ ትራምፕ ‘ፕሮፔሺያ’ የተሰኘ የፀረ ራሰ-በራነት መድኃኒት እንደሚወስዱ መዘገቡ ይታወሳል።

እኒህ ሐኪም ታዲያ ከሰሞኑ ወደ ዓለማቀፍ መገናኛ ብዙኃን ብቅ ብለው ያልተሰሙ መረጃዎችን መስጠት ጀምረዋል።

ከነዚህ መረጃዎች አንዱ አወዛጋቢው ዶናልድ ትራምፕ የሪፐብሊካን እጩ ሳሉ “እጅግ ጤነኛው ፍጡር” ስለመሆናቸው የሚያትተውን የሐኪም መግለጫ ትራምፕ ራሳቸው እንደጻፉት ማጋለጣቸው ነው።

የግል ሐኪማቸው ሐሮልድ ከሲኤንኤን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ልዩ ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት ፕሬዚዳንቱ ስለ ጤናቸው የምስክር ወረቀቱን የሚጽፉት ራሳቸው ነበሩ።

ዋይትሐውስ በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም።

ሐኪም ሐሮልድ ጨምረው በጥቅምት 2017 ክሊኒካቸው ድንገት በትራምፕ የግል ጠባቂዎች ለሰዓታት መበርበሩንና ስለ ትራምፕ ጤንነት የሚያወሱ ዶሴዎች በሙሉ መዘረፋቸውን ተናግረዋል።

በ2015 በወጣ አንድ ሰነድ ያኔ እጩ የነበሩት ትራምፕ ከተመረጡ «እስካዛሬ ከነበሩ የአሜሪካ መሪዎች ሁሉ በፍጹም መልካም ጤንነት ላይ የሚገኙት መሪ» እንደሚሆኑ የሚተነብይ ሐተታ በኚሁ ሐኪም ስም ወጥቶ ነበር። ሆኖም ይህን ሐተታ “ራሳቸው ትራምፕ እንጂ እኔ አልጻፍኩትም” ሲሉ ሐኪሙ አስተባብለዋል።

ሐኪም ሐሮልድ ይህንን ክስና አቤቱታ ለምን አሁን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ እንደፈለጉ የታወቀ ነገር የለም።

የሕክምና ማስረጃው ምን ይዟል?

በወቅቱ ስለ ትራምፕ ጤንነት በሚያትተው ማስረጃ ላይ ዶናልድ ትራምፕ ባልተለመደ ሁኔታ ‘ፍጹም ጤናማው መሪ’ እንደሚሆኑ በተደጋጋሚ ያትት ነበር።

 
የደም ግፊታቸው እና የላቦራቶሪ ናሙና ውጤታቸው "ከየትኛውም በሽታ ፍጹም የፀዱ" የሚል ውጤትን ይዞ ነበር።

በአንድ ዓመት ብቻ ክብደታቸው በ7 ኪሎ ግራም መቀነሱን በመጥቀስ ፕሬዚዳንቱን ያሞካሻል ሪፖርቱ።

ከዚህም ባሻገር ትራምፕ ምንም ዓይነት የካንሰር ምልክት ወይም የመገጣጠሚያ ሕመም ድርሽ ብሎባቸው እንደማያውቅም ያወሳል።

ይህ የጤና ሁኔታቸውን የሚያትተው መግለጫ ይፋ ከመደረጉ ቀደም ብሎ ትራምፕ በፌስቡክና በትዊተር ገጻቸው ላይ ሐኪማቸው ከበሽታዎች ሁሉ የጸዱ ስለመሆናቸው እንደመሰከሩላቸው ገልጠው ነበር።

“በሽታን የማያውቅ የዘር ቅንጣት ስለታደልኩ ዕድለኛ ነኝ” ሲሉም በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አሥፍረው ነበር።

ትራምፕ በአሜሪካ ታሪክ በዕድሜ እጅግ የገፉ መሪ እንደሆኑ ይታወቃል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.