የጋሬዝ ክሩክስን የሳምንቱን ምርጥ ቡድን ለመቀለላቀል የትኞቹ ተጫዋቾች ድንቅ ብቃት አሳዩ?

                     በሳምንቱ መጨረሻ የተካሄዱት የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫና ፕሪሚዬር ሊግ ፍልሚያዎች በርካታ ድንቅ ተጫዎቾችን አሳይተውናል። ከእነዚህ መሃል ነጥረው ወጥተው የተንታኙ ጋሬዝ ክሩክስን ቀልብ መሳብ መቻል የቻሉት እነማን ይሆኑ?

ግብ ጠባቂ – ዌ ሄንሴይ (ክሪስታል ፓላስ)

ዌይን ሄንሴይImage copyrightGETTY IMAGES

ካለ ግብ በተጠናቀቀው የክሪስታል ፓላስና የዋትፎርድ ጨዋታ ግብ ጠባቂው ዌይን ሄንሴይ ድንቅ ብቃትን በማሳየት ቡድኑን ታድጓል። ሄንሴይ አምስት ግብ ሊሆኑ የሚችሉ ኳሶችን በማዳን፤ ቡድኑ ክሪስታል ፓላስ ከ12 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግብ ያላስተናገዱበትን ሁለተኛ ጨዋታ ማሳካት አስችሏል።

ተከላካዮች – ሴዛር አዝፒሉኬታ (ቼልሲ), ክሪስ ስሞሊንግ (ማንቸስተር ዩናይትድ), ናቾ ሞንሪያል(አርሰናል)

ሴዛር አዝፒሉኬታ (ቼልሲ), ክሪስ ስሞሊንግ (ማንቸስተር ዩናይትድ), ናቾ ሞንሪያል (አርሰናል)Image copyrightGETTY IMAGES

ሴዛር አዝፒሉኬታ-ቼልሲዎች ከሳውዝሃምፕተን ጋር ባደረጉትየኤፍ ኤ ካፕ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታ፤ አዝፒሉኬታ ለአልቫሮ ሞራት ሲያሻግራቸው የነበሩት ኳሶች አስገራሚ ነበሩ።

ክሪስ ስሞሊንግ- በሌላኛው የኤፍ ኤ ካፕ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታ የማንቸስተር ዩናይትዱ የመሃል ተከላካይ ስሞሊንግ ድንቅ ብቃቱን ማሳየት ችሏል። የቶተንሃሙን ሃሪ ኬንንም መፈናፈኛ ኣሳጥቶት ነበር።

ናቾ ሞንሪያል- በአርሰናል 4 ለ 1 አሸናፊነት በተጠናቀቀው የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ፤ ሞንሪያል አንድ ጎል ማስቆጠር ችሏል። በመከላከሉ ረገድም የነበረው አስተዋጽኦ ቀላል አልነበረም።

አማካዮች- አንዴር ሄሬራ (ማንቸስተር ዩናይትድ)፣ ኬቪን ደ በ (ማንቸስተር ሲቲ)፣ ፖል ፖግባ (ማንቸስተር ዩናይትድ)፣አሌክሲስ ሳንቼዝ (ማንቸስተር ዩናይትድ)

አንዴር ሄሬራ -ማንቸስተር ዩናይትድ ከቶተንሃም ጋር ባደረገውየኤፍ ኤ ካፕ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ሄሬራ የቶተንሃሙን ዴምቤሌን መቆጣጠር ችሎ ነበር። ቀደም ባሉት ሁለት የኤፍ ኤ ጨዋታዎች ላይ ግብ ማስቆጠር የቻለ ሲሆን በዚህኛውም ጨዋታ የማሸነፊያዋን ጎል አስቆጥሯል።

ን ደ በነ- በእሁዱ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ የደበራይነ እና የዴቪድ ሲልቫ ጥምረት ድንቅ ነበር። ደበራይነ ያስቆጠራት ግብ ደግሞ እጅግ በጣም የተለየች ነበረች። በዚህ ውድድር ወቅት ከማንኛውም ተጫዋች በላቀ ሁኔታ ደ በራይነ አምስት ግቦችን ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውጪ ማስቆጠር ችሏል።

ፖል ፖግባ– በቅዳሜው የኤፍ ኤ ካፕ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታ፤ ፖግባ ለአሌክሲ ሳንቼዝ አሻግሮለት የተቆጠረችው ግብ ድንቅ ነበረች ።በተጨማሪም ለሮሜሉ ሉካኩ እና ጄሲ ሊንጋርድ አመቻችቶ ያቀበላቸው ኳሶች የተጫዋቹን ብቃት ያስመሰከሩ ነበሩ።

አንዴር ሄሬራ (ማን ዩናይትድ)፣ ኬቪን ደ በራይነ (ማን ሲቲ)፣ ፖል ፖግባ (ማን ዩናይትድ)፣አሌክሲስ ሳንቼዝ (ማን ዩናይትድ)Image copyrightGETTY IMAGES

አጥቂዎች- ሞሃመድ ሳላህ (ሊቨርፑል)፣ ሶሎሞን ሮንዶን (ዌስት ብሮም)፣ ዳኒ ኢንግስ (ሊቨርፑል)

ሞሃመድ ሳላህ (ሊቨርፑል)፣ ሶሎሞን ሮንዶን (ዌስት ብሮም)፣ ዳኒ ኢንግስ (ሊቨርፑል)Image copyrightGETTY IMAGES

ሞሃመድ ሳላህ – በአንድ የውድድር ወቅት ይህ ተጫዋች ያስቆጠራቸው 41 ግቦች አንዳንድ የፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች ካስቆጠሩት ይበልጣል። ቅዳሜ ዕለት በፕሪምየር ሊጉ ያስቆጠራት 31ኛ ግብም ተጨማሪ የብቃቱ ማሳያ ሆናለች።

ሶሎሞን ሮንዶን – ይህ የዌስት ብሮም አጥቂ ፕሪምየር ሊጉን አይመጥንም እስከማለት ደርሼ የነበረ ቢሆንም በዕሁዱ ጨዋታ ያሳየው ብቃት ግን የአርሰናሉን ላካዜት በመተው እሱን እንድመርጠው አድርጎኛል ይላል ክሩክስ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement