ናሳ ከመሬት ጋር የሚመሳሰል ፕላኔት ፍለጋ አዲስ መንኮራኩር ሊያመጥቅ ነው

                      

ናሳ ከመሬት ጋር የሚመሳሰል ሌላ ፕላኔት ፍለጋ መንኩራኩር ሊያመጥቅ መሆኑ ተሰምቷል።

የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ማእከል የሆነው ናሳ አዲስ የሚያመጥቀው መንኮራኩር “ቴስ” የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን፥ በመሬት ዙሪያ የሚገኙ ፕላኔቶች ላይ አሰሳ እንደሚያደርግም ተነግሯል።

መንኮራኩሩም አስከ 200 ሺህ የሚደርሱ ከዋክብቶችን የብርሃን መጠን በመለካት እስከ 20 ሺህ የሚደርሱ አዳዲስ ፕላኔቶችን ማግኘት አንደሚቻልም ናሳ ተስፋ አደርጓል።

ከሚገኙት ውስጥም 500 የሚደርሱትፕላኔቶች ነብስ ላላቸው ነገሮች ለኑሮ ተስማሚ ሊሆኑ ይችላሉም ብሏል።

ናሳ ከዚህ ቀደም ለመኖር አመቺ የሆኑ ከመሬት ጋር የሚመሳሰሉ ፕላኔቶችን ለማፈላለግ “ክለፐር” የተባለ መንኮራኩር ሲጠቀም ቆይቷል።

ሆኖም ግን አሁን እንደ አዲስ የሚመጥቀው “ቴስ” የተባለው አዲሱ መንኮራኩር “ክለፐር” ከተባለው መንኮራኩር በ400 እጥፍ በሚበልጥ የማፈላለግ ስራ ይሰራል ነው የተባለው።

“ክለፐር” ከተባለው መንኮራኩር ለ9 ዓመታት በነበረው ቆይታ 2 ሺህ 343 ከፕላኔት ጋር የሚመሳሰሉ ነገሮችን ያገኘ ሲሆን፥ ከእነዚህም ወሰጥ 30ዎቹ ከመሬት ጋር የተቀራረበ ቅርጽ እንዳላቸውም ተለይተዋል።

በአሁኑ ወቅት ግን “ክለፐር” መንኮራኩር ነዳጅ እየጨረሰ በመምጣቱ እና ስራውንም በአግባቡ መከወን ስለተሳነው “ቴስ” በተባለው መንኮራኩር ተተክቷል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement