በአሜሪካ በበሽታ ስጋት 207 ሚሊየን እንቁላሎች ከዘጠኝ ግዛቶች እንዲሰበሰቡ ታዘዘ

                 

በዩናይትድ ስቴትስ ኢንዲያና ግዛት ውስጥ የሚገኝ የዶሮ እርባታ 207 ሚሊየን የሚደርሱ እንቁላሎች ከዘጠኝ ግዛቶች እንዲሰበሰቡ አዘዘ።

ዕንቁላሎቹ ተቅማጥ፣ ራስምታት እና የሆድ ህመምን በሚያስከተል “ሳልሞኔላ” በተባለ ባክቴሪያ ተበክለዋል በሚል ስጋት ነው እንዲሰበሰቡ የታዘዘው።

የሀገሪቱ የምግብና የመድሐኒት ተቆጣጣሪው መስሪያ ቤት እስከአሁን በባክቴሪያ 22 ሰዎች ተይዘው መታመማቸውን አስታውቋል።

ሮዝ አክሪ የተባለው ድርጅት ዕንቁላሎቹ ለአከፋፋዮችና ለምግብ ቤቶች መሸጣቸው የተነገረ ሲሆን፥ ዘጠኝ ግዛቶች ውስጥ እንደተዳረሰም ተመልክቷል።

መስሪያ ቤቱ በዘጠኙ ግዛቶች ውስጥ ለሚኖሩ ነዋሪዎች ዕንቁላሉን እንዳይመገቡ አስጠንቅቋል።

ባክቴሪያው ከስጋ እና ከውሃ እንደሚመጣ የታወቀ ሲሆን፥ እንዲሁም የባክቴሪያው ተጠቂ የሆነች ዶሮ ወደ እንቁላሉ ታስተላልፋለች ነው የተባለው።

ባክቴሪያው ከሰው ወደ ሰው በምራቅ እንዲሁም በመሳሳም እንደሚተላለፍ ተገልጿል።

ይህ ባክቴሪያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2010 በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለህመም የዳረገ መሆኑና ግማሽ ቢሊየን ዕንቁላሎች እንዲሰበሰቡ ምክንያት መሆኑም የሚታወስ ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement