መመላለስ ያለብን ይህን ያህል ጊዜ ነው የሚል የተቀመጠ መስፈርት ባይኖርም ሰዎች በቀን ቢያንስ በአማካይ ለስድስትና ለሳባት ጊዜያት ያህል ይመላለሳሉ ይላሉ ባለሙያዎች።
በእርግጥ የተለያዩ ምክንያቶች ምልልሳችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ ከነዚህም መካከል መድሐኒት፣ ምግብና መጠጥ፣ ዕድሜ፣ የሽንት ፊኛ መጠን እና ሌሎችም ተካተዋል።
ታዲያ ይህንን ካልን ዘንድ ጤነኛና ጤነኛ ያለሆነ ምልልስን ምልክቶቹ ምን እንደሚመስሉ እንቃኝ፤
ጤነኛ የሽንት ምልልስ አንድ ሰው በ24 ሰዓታት ውስጥ 1 ነጥብ ዘጠኝ ሊትር ከተጠቀመ ለሰባት ጊዜያት ያህል ሊመላለስ ይችላል ይላል።
ሆኖም ከላይ ከጠቀስናቸው ተጽዕኖዎች በተጨማሪ የምንወስዳቸው የመጠጥ ዓነቶች እንደ አልኮልና አነቃቂ መጠጦች ከሆኑ የሽንት መጠንን ይበልጥ ይጨምራሉ።
እንዲሁም አንዳንድ መድሐኒቶች በተለይ ለደም ግፊት የምንወስዳቸው የሽንት መጠን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ ተብሏል።
በእርግዝና ወቅት የሚመጣ በሆርሞን ለውጥ ምክንያት የሚከሰት የሽንት መጨመርም ሊያጋጥም ይችላል።
እንዲሁም ከወሊድ በኋላ ለስምንት ሳምንታት ሊቆይ እንደሚችልም ይናገራሉ።
ለሽንት ቶሎ ቶሎ መመላለስና ያለመመላለስ ያለንበት ሁኔታን ያመላክታሉ ከተባሉት መካከል የጀርባ ህመም፣ ደም የቀላቀለ ሽንት፣ ለመሽናት መቸገር፣ ራስ ምታት፣ ከባድ ሽታ ያለው እና በሽንት ወቅት የህመም ስሜት መሆናቸው ተገልጿል።
ታዲያ ከላይ የተዘረዘሩት ምልክቶች ካጋጠማችሁ የህክምና ባለሙያ ማማከር አለባችሁ ይላሉ ባለሙያዎች።
በሌላ በኩል ብዙ ውሃ መጠጣት የሽንት መጠናችንን ቢጨምረውም በተቃራኒው ውሃ ያለመጠጣት ደግሞ ድርቀትን ያስከትላል።
ዕድሜ እየጨመረ ሲሄድ በምሽት ተነስተን የመሽናት ዕድላችን እየጨመረም ይሄዳል ብለዋል ባለሙያዎቹ።
በተጨማሪም ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆናቸው ሰዎች ከሁለት ጊዜ በላይ መነሳት የለባቸውም፤ ሆኖም ከሁለት ጊዜ በላይ ከተነሱ ሐኪምን ማማከር ማማከር ይገባል።
ታዲያ የሽንት መጠናችንን ለመቆጣጠር የተቀመጡ አንዳንድ መስፈርቶች ተጠቅሰዋል።
ከነዚህም መካከል የአነቃቂ መጠጦችን መጠን መቀነስ፣ ስምንት ብርጭቆ ውሃ በቀን መጠጣት፣ ከግብረስጋ ግንኙነት በፊትና በኋላ መሽናት፣ እንደ እርጎ ያሉ ምግቦችን መቀነስ እና ሌሎችም ተጠቅሰዋል።
ባለሙያዎቹ በምንሸናበት ወቅት በመሐል ቢያንስ የሦስት ሰዓታት ልዩነት መኖር አለበት ብለዋል።