ጂሜይል ማሻሻያ ሊደርግበት ነው

                  

ጉግል ኩባንያ የኤሌክትሮኒክስ መልዕት መለዋወጫን(ጂሜይል) ለተጠቃሚዎች ምቹ ለማድረግና በአዲስ አቀራረብ ለማምጣት መሻሻያ ሊደረግበት መሆኑን አስታወቀ።

ይህንንም ጉግል ጂ ስዊት አገልግሎትን ለሚጠቀሙ ደንበኞቹ ማሳወቁ ተነግሯል።

ማሻሻያው ከሚያካትታቸው ጉዳዮች መካከል የጉግል ካላንደር በመልዕት መለዋወጫው ማግኘት ማስቻል ይገኝበታል።

ከሚገቡ መልዕከቶች መካከል መልስ ያልተሰጣቸው መልዕክቶች እንዲሰጣቸው የማስታወስ ተግባርንም ያካትታል።

እንዲሁም ከአንድ ተግባር በላይ መከወን የሚያስችል አማራጭ፣ ፈጣን መልዕክት መመላሻ እና መልዕክት ማስቀመጫ መተግበሪያ በሚሻሻለው ጂሚል ይካተታልም ተብሏል።

ይህም በዓለም ላይ ከሚገኙ የኤሌከትሮኒክስ መልዕክት መለዋወጫ አገልግሎትን ከሚያቀርቡት ኩባንያዎች ማሻሻያ በማድረግ ቀዳሚው ያደርገዋል ተብሏል።

ማሻሻያውም ለልዩ ደንበኞች ከደረሰ በኃላ ወደ መደበኛ ተጠቃሚዎች እንደሚደርስ ነው የተነገረው።

ሆኖም ጉግል ኩባንያም ማሻሻያው በጅምር ላይ እንደሚገኝ ያስታወቀ ሲሆን፥ ተግባራዊ ለማድረግ ግዜ እንደሚስፈልግ አስታውቋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement