ኢትዮጵያዊቷ የሙሽሪቶች ፋሽን ዲዛይነር አምሳለ አበራ ከዚህ አለም በሞት ተለየች – Hollywood’s bridal-wear designer Amsale Aberra passes away at 64

 

ኢትዮጵያዊቷ የሙሽሪቶች ፋሽን ዲዛይነር አምሳለ አበራ ከዚህ አለም በሞት ተለየች::

በተለይ የሠርግ ልብስ ዲዛይኖችን በመስራት ለአሜሪካውያንና ለሌሎችም ታላላቅ ሰዎች በማቅረብ የምትታወቀው አምሳለ አበራ ያረፈችው ትናንት ምሽት ነው። አድማስ ሬዲዮ ባገኘው መረጃ፣ አምሳለ ለጥቂት ጊዜ በህመም ላይ ቆይታለች። ከወይዘሮ ጸዳለ አሳምነው እና ከአቶ አበራ ሞልቶት አዲስ አበባ ውስጥ ነው የተወለደችው። በልጅነቷ ወደ አሜሪካ መጥታ በፖሊቲካል ሳይንስና በፋሽን ዲዛይን ሁለት ዲግሪዎችን አግኝታለች። ባለትዳርና የአንዲት ልጅ እናት ነች.:

Source: Admas radio

Advertisement