በግብፅ ለሦስት ቀናት የሚቆየው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተጀመረ

                   

በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በከፍተኛ ድምፅ ይመረጡበታል ለተባለው ምርጫ ግብፃዊያን ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ድምፅ መስጠት ጀመሩ።

አብዛኞቹ የተቃዋሚ ዕጩዎች እራሳቸውን ከፕሬዝዳንታዊው ውድድር በማግለላቸው ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ማሸነፋቸው አጠራጣሪ አይደለም ተብሏል።

ብቸኛው በውድድሩ ውስጥ ያሉት ተፎካካሪ ብዙም የማይታወቁት ሙሳ ሙስጠፋ ናቸው።

ተፎካካሪው ሙሳ በፕሬዝዳነት ሲሲ ደጋፊነት የሚታወቁ ሲሆን፤ በድጋሚ መመረጣቸውንም እንደሚደግፉ ሲናገሩ ተደምጠዋል።

መጀመሪያ ላይ ሰባት እጩዎች ፕሬዝዳንት ሲሲን ለመፎካከር ቀርበው የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ ግን አብዛኞቹ እራሳቸውን ከምርጫው አግልለዋል።

ከፕሬዝዳንታዊው ምርጫ እራሳቸውን ካገለሉት መካከል የቀድሞው የሃገሪቱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ሻፊቅ እና የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ጠበቃ የሆኑት ካሊድ አሊ የደረሰባቸውን ማስፈራሪያ ጠቅሰው ከምርጫው ወጥተዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement