ለአየር ንብረት ለውጥ የበለጠ ተጋላጭነት ያላቸው አራት የእስያ አገራት

                      

ህንድ፣ ፓኪስታን፣ ፊሊፒንስ እና ባንግላዴሽ ለአየር ንብረት ለውጥ የበለጠ ተጋላጭነት ያላቸው የእስያ ሀገራት መሆናቸው አንድ ሪፖርት አስታወቀ።

ኤች ኤስ ቢ ሲ በሚል ምህፃረ ቃል የሚታወቀው ዓለም አቀፋዊ የባንክ እና የገንዘብ አገልግሎቶች ድርጅት ይፋ ያደረገው ሪፖርት እንዳመለከተው፥ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ሙቀት መጨመር በአምስት ሀገሮች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሯል። 

በዚህም በአየር ሙቀት መጨመር ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ከተጎዱ ሀገሮች አራቱ የእስያ ሲሆኑ ኦማን በአምስተኛ ደረጃ ተቀምጣለች። 

ባንኩ ኢኮኖሚያቸው ያደገ እና በማደግ ላይ ባሉ 67 ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ ካላቸው ተጋላጭነት በማያያዝ ጥናት አካሂዷል። 

ይህም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖዎች፣ የአየር መዛባት ተለዋዋጭ ሁኔታዎች፣ ተጋላጭነት እና ለአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ የመስጠት ችሎታ በሚመለከት ጥናቱ ዳስሷል።

በዚህም ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ ከተባሉ አራቱ የእስያ ሀገሮች ውስጥ ህንድ በበለጠ የአየር ንብረት ለውጡ የእርሻ ገቢዋን እንደሚቀንሰው አመላክቷል።

በተለይም በመስኖ ያልለሙ አከባቢዎች በሙቀት መጠን መጨመር እና በዝናብ መጠን መቀነስ ምክንያት የከፋ ጉዳት እንደሚደርሳቸው ተነግሯል። 

ፓኪስታን፣ ባንግላዴሽ እና ፊሊፒንስ ለአውሎ ነፋስ፣ ለጎርፍ መጥለቅለቅ የመሳሰሉ የአየር ንብረት ክስተቶች በጣም የተጋለጡ ናቸው።

ከዚህ ባለፈ ኦማን፣ ስሪ ላንካ፣ ኮሎምቢያ፣ ሜክሲኮ፣ ኬንያ እና ደቡብ አፍሪካም ለአየር ንብረት ተጋላጭ ናቸው ከተባሉ 10 ሀገሮች መካከል ይገኛሉ።

ሮይተርስ ዋቢ በማድረግ ሲጂቲኤን እንደዘገበው ፊንላንድ፣ ስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ኤስቶኒያ እና ኒውዚላንድ ለአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸው ሀገሮች ናቸው።

ሪፖርቱ ጥናት ከተደረገባቸው 67 ሀገሮች ከአውሮፓውያኑ 2006 እስከ 2016 ድረስ ለአንድ ሰው ከሚያስፈልገው የውኃ አቅርቦት በአማካይ 10 በመቶ መድረሱን አመልክቷል። ይህም ኩዌት የነፍስ ወከፍ የውሃ አቅርቦቷ እጅግ ዝቅተኛ እንደነበር አንስታል።

ሪፖርቱ እንዳስታወቀው ሲንጋፖር እና የዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ ዝቅተኛ የነፍስ ወከፍ የውሃ አቅርቦት ይኖራቸዋል።

በቅርቡ የወጣው የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያሳየው፥ የአየር ንብረት ለውጥ በሶስት የዓለም ክፍሎች ወይም አከባቢዎች ላይ ስደትን ያስከትላል።

ለዚህም ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት 86 ሚሊየን ህዝብ የሀገር ውስጥ መፈናቀል ሊገጥማቸው ይችላል።

40 ሚሊየን የሚሆኑ ደግሞ በደቡብ እስያ ተመሳሳይ ዕጣ እንደሚገጥማቸው እና በላቲን አሜሪካም 17 ሚሊየን ህዝብ ሊፈናቀል እንደሚችል ተንብየዋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement