የካርቦን ልቀትን በመቀነስ ብቻ የ153 ሚሊየን ሰዎችን ህይወት መታደግ ይቻላል – ጥናት

                               

የካርቦን ልቀትን በመቀነስ ብቻ የ153 ሚሊየን ሰዎችን ህይወት መታደግ እንደሚቻል አዲስ የተሰራ ጥናት አመልክቷል።

በአሜሪካ ካሮላይና የዱክ ዩኒቨርሲቲ ጥናት እንዳመለከተው፥ መንግስታት የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ ያስቀመጡትን እቅድ ቶሎ ተግባራዊ ማድረግ ከቻሉ በዓለም ላይ ያለ እድሜ የሚከሰት የ153 ሚሊየን ሞትን መከላከል ይቻላል።

ጥናቱ የካርበን ልቀትን መቀነስ ከተቻለ የምን ያክል ሰዎችን ህይወት መታደግ ይቻላል በሚል በቁጥር የለየ የመጀመሪያ መሆኑ ተነግሯል።

ጥናቱ በካርበን ልቀት ምክንያት በእያንዳንዱ የዓለም ከተሞች ምን ያክል ሀይወትን መታደግ ይቻላል የሚለውን የለየ ሲሆን፥ የ154 ከተሞችን አሃዝም በዝርዝር አስቀምጧል።

የካርበን ልቀትን መቀነስ ተግባራዊ ሲደረግ ተጠቃሚ ከሚሆኑ ከተሞች ውስጥ የአፍሪካ እና የእሲያ ከተሞች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉም ተብሏል።

በህንዶቹ ከልካታ እና ዴልሂ ከተሞች ብቻ የካርበን ልቀት መቀነስ በ4 ነጥብ 4 ሚሊየን እና በ4 ሚሊየን ሰዎች ላይ ያለእድሜ የሚከሰት ሞትን ማስቀረት እንደሚቻል ጥናቱ ግምቱን አስቀምጧል።

እንዲሁም 13 የሚደርሱ የአፍሪካ እና የእስያ ሀገራት ከተሞች ላይም የካርበን ልቀትን በመቀነስ በእያንዳንዳቸው ከተሞች እስከ 1 ሚሊየን የሚደርስ ያለ አድሜ የሚከሰት ሞትን መከላከል ይቻላል ብሏል ጥናቱ።

80 በሚደርሱ ተጨማሪ ከተሞች ላይ ደግሞ በእያንዳንዳቸው እስከ 100 ሺህ የሚደርስ ያለ እድሜ የሚከሰት ሞትን የካርበን ልቀትን በመቀነስ ብቻ መከላከል ይቻላል የሚለውንም ጥናቲ አመልክቷል።

እንደ ሞስኮ፣ ሜክሲኮ ሲቲ፣ ሳኦ ፖሎ፣ ኦስ አንጀለስ፣ ፑዌልባ እና ኒው ዮርክ ባሉ ከተሞች ደግሞ በእያንዳንዳቸው ከ320 ሺህ እስከ 120 ሺህ ሰዎች ላይ ያለ እድሜ የሚከሰት ሞትን ማስቀረት እንደሚቻልም ተጠቁማል።

ጥናቱን ያካሄዱት ተመራማሪዎች፥ በጥናቱ ይፋ የተደረገው መረጃ ፖሊሲ አውጪዎች እና ህብረተሱ የካርበን ልቀትን መቀነስ ምን ያክል ጠቀሜታ እንዳለው በቀላሉ እንዲረዱ ያስችላቸዋል ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement