“ለቻይና የሚያዋጣት ሶሻሊዝም ነው” ዢ ጂንፒንግ

                     

የቻይናው ፕሬዚደንት ዢ ጂንፒንግ ለገዢው የህዝቦች ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ አባላት ንግግር ባደረጉበት ወቅት ቻይና ባሳየችው ዕድግት አጉል የራስ መተማመን ሊሰማት አይገባም ሲሉ ተደምጠዋል።

በዓመታዊው የቻይና ፓርላማ ስብሰባ መዝግያ ላይ ንግግር ያሰሙት ዢ ቻይና አሁን ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢ ከመሆኑ አንፃር ከሶሻሊዝም ፈቀቅ ልትል አይገባም ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

ምንም እንኳ ከዜጎች ተቃውሞ ቢገጥመውም ገዢው የህዝቦች ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ በያዝነው ዓመት የፕሬዚደንቱን የስልጣን ዘመን ገደብ ማንሳቱ የሚታወስ ነው።

ውሳኔው የወቅቱ መሪ የሆኑት ዢ ጂንፒንግ የሕይወት ዘመን ፕሬዚደንት እንዲሆኑ ኃይል ይሰጣቸዋል።

የቻይና ፓርላማ በዓመት አንድ ጊዜ የሚሰበሰብ ሲሆን በገዢው ፓርቲ ውሳኔ የተሰጠባቸውን ርዕሰ ጉዳዮች ማፅደቅ ዋነኛ ተግባሩ ነው።

በዘንድሮ ስብሰባ ማጠናቀቂያ ድመፃቸውን ለሃገራቸው ህዝብ ያሰሙት ዢ ቻይና ‘ለሰው ልጅ ስልጣኔ እያበረከተች ያለችውን አስተዋፅኦ’ ካሞካሹ በኋላ ሃገራቸውን የበለጠ ለማዘመን ዕቅድ እንዳላቸው አሳውቀዋል።

አልፎም ቻይና ማደግ ካለባት አንድነት አስፈላጊነቱ የጎላ መሆኑን በማስመር እንደ ታይዋን ሁሉ ማንኛውም ኃይል ለመገንጠል የሚያደርገውን ሙከራ ቤይዢንግም በትዕግስት እንደተማትመለከተው አሳስበዋል።

ህግ አውጭዎች አዲስ የፀረ ሙስና ያረቀቁ ሲሆን በቻይና ማዕከላዊ ባንጅ አስተዳደርና በምጣኔ ሃብት አማካሪው የሚመራ ወኪል (ኤጀንሲ) ማቋቋማቸውንም አስታውቀዋል።

ይህ የፓርላማ ስበስባ በአምስት ዓመታት አንድ ጊዜ የሚካሄደውን የኮሚኒስት ፓርቲ ኮንግረስ ስብሰባ ተከትሎ የተካሄደ ሲሆነ ታዛቢዎች ፓርቲው ወትሮም ጠንካራ ለነበሩት ዢ ጂንፒንግ እንደ ማዖ ዜዱንግ ያለ ግዙፍ ሥፍራ እንደሰጣቸው ይናገራሉ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement