የአሜሪካ ደቡብ ኮሪያና የጃፓን የጸጥታ አማካሪዎች በሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ላይ እየመከሩ ነው

                                    

በአብረሃም ፈቀደ

የአሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያና የጃፓን ከፍተኛ ብሄራዊ የጸጥታ አማካሪዎች በሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ላይ እየመከሩ ነው።

የፀጥታ አማካሪዎቹ በሰሜን ኮሪያ እና የኮሪያን ልሳነ ምድር ከኒውክሌር ቀጠና ነጻ ማድረግ በሚቻልበት አግባብ ላይ እየመከሩ መሆኑን፥ ከደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግስት የወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።

በውይይታቸው በኮሪያ ልሳነ ምድር ያለፈውን ስህተት መድገም እንደማይገባም አጽንኦት ሰጥተው መክረዋል።

ከሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ባሻገርም አማካሪዎቹ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና የሰሜን ኮሪያው አቻቸው ኪም ጁንግ ኡን ተገናኝተው የሚወያዩበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ያለመ ምክክርም ያደርጋሉ።

ከዚህ ባለፈም የደቡብ ኮሪያና የሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንቶች በደቡብ ኮሪያው ሰማያዊ ቤተ መንግስት ተገናኝተው መወያየት በሚችሉባቸው አግባቦች ላይም ይመክራሉም ነው የተባለው።

የሰሜን ኮሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከስዊድኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በጸጥታ ጉዳይ ላይ ለሦስት ቀናት የዘለቀ ምክክር ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡

ይህን ተከትሎም ትናንት እሁድ ከፍተኛ የሰሜን ኮሪያ ባለስልጣናት ልዑክ ከቀድሞ የአሜሪካና የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት ጋር ለመወያየት ወደ ፊንላንድ ማቅናቱም ተገልጿል፡፡

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement