ኳታር ከጣሊያን 28 ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮችን ለመግዛት የ3 ቢሊየን ዩሮ ስምምነት ተፈራረመች

                                   

ኳታር ከጣሊያን 28 ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮችን ለመግዛት የ3 ቢሊየን ዩሮ ስምምነት ተፈራረመች።

ኳታር ኤን ኤች 90 የተሰኙትን ሄሊኮፕተሮች ሊዮናርዶ ከተባለው የጣሊያን የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ እንደምትገዛ የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒሰተር አስታውቋል።

ሊዮናርዶ የመጀመሪያዎቹን ሄሊኮፕተሮች በሰኔ 2022 የሚያቀርብ ሲሆን፥ እስከ 2025 ሁሉንም አጠናቆ ለኳታር ያስረክባል።

በኳታር የኢሚሪ አየር ኃይል የሄሊኮፕተር ክንፍ አዛዥ የሆኑት ማሾት ፊሳል አል ሃጅሪ፥ የኳታር አየር ኃይል ያለውን ብቃት ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል።

በተጨማሪም ዶሃ ሬይሰን ከተባለ የአሜሪካ ወታደራዊ ኮንትራክተር ጋር በሳይበር ደህንነት ተባብሮ መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

በሳኡዲ እና የባህረ ሰላጤው ሀገራት መገለል የደረሰባት ኳታር በቅርቡ ከሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ ጋርም በወታደራዊ ዘርፎች ተባብሮ ለመስራት መስማማቷን ይታወሳል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

Advertisement