የደም ግፊት፣ በደም ውስጥ ያለን ስብ ለመቀነስ፣ ኢንፌክሽንና ጉንፋንን ልንከላከል የምንችልባቸው መንገዶች

                              

ነጭ ሽንኩርት፣ ሎሚ እና ዝንጅብል በዉሃ ውስጥ አንድ ላይ ደባልቆ መጠቀም የደም ግፊት፣ በደም ውስጥ ያለ ስብን ለመቀነስ እንዲሁም ኢንፌክሽንና ጉንፋንን ለመከላከል እንደሚረዳ ከወደ ጀርመን ሀገር የወጣ መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅምም ከፍ እንዲል እንደሚረዳም ተጠቁሟል።

ውህዱን ለማዘጋጀት የሚስፈልጉን ነገሮች

አራት ራስ ነጭ ሽንኩርት፣ አራት ያልተላጠ ሎሚ፣ አነስ ያለ ዝንጅብል እንዲሁም ሁለት ሊትር ዉሃ።

አዘገጃጀት

ሎሚውን አጥበን መቆራረጥ፣ ነጭ ሽንኩርቱንና ዝንጅብሉን ልጠን አንድ ላይ መደባለቅ።

በመቀጠል ከብረት የተሰራ ጎድጓዳ ሰሃን ውስጥ በመጨመር እና ሰሃኑ ውስጥ ሁለት ሊትር ውሃ በመጨመር አንድ ላይ ማፍላት።

የፈላው ውሃ ለብ እስኪል በመጠበቅ በውሃ መጠጫ ብርጭቆ አድርጎ መጠጣት።

የነጭ ሽንኩርት፣ ሎሚ እና ዝንጅብል ውህዱን በየቀኑ ጠዋት ምግብ ከመመገባችን ከሁለት ሰዓት በፊት በባዶ ሆድ መጠጣት ይመከራል።

ከመጠጣታችን በፊት ውህዶቹ ከስር ዘቅጠው እንዳይቀሩ ለመደባለቅ መወዝወዝ ይኖርብናል።

 

ምንጭ፦Mahdere Tena

 

Advertisement