ኩላሊት ሲጎዳ የሚታዩ 8 ምልክቶች

                                  

ኩላሊት ሲጎዳ የሚታዩ 8 ምልክቶች

  1. የትንፋሽ ማጠር፤ ኩላሊታችን ችግር ሲያጋጥመው የቀይ ደም ህዋስ ቁጥር ስለሚቀንስ ትንፋሽ ሊያሳጥረን ይችላል
  2. ምላሳችን ላይ የብረት ጣዕም መሰማት፤ የኩላሊት ችግርን ተከትሎ በደም ውስጥ የንጥረ ነገሮች ይዘት ላይ ለውጥ ስለሚኖር በምላሳችን ላይ የብረት ጣዕም ከመሰማትን ጀምሮ እስከ ጠቅላላ የምግብ ጣዕም ለውጥ ሊኖር ይችላል፡፡ የደም ይዘት ለውጥን ተከትሎ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ችግርም ያጋጥማል፡፡
  3. የውሃ ሽንት ከለር ለውጥ፤ የሽንት ከለር ለውጥ አንዱ የኩላሊት ጉዳት ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይም የውሃ ሽንት ከለር ጠቆር ወዳለ ብጫ ከለር በተደጋጋሚ ከተስተዋለ የኩላሊት ጉዳት ውጤት ሊሆን ይችላል፡፡
  4. የትኩረት መቀነስ፤ የኩላሊት መጎዳት ኦክሲጅን በአግባቡ ወደ ጭንቅላት እንዳይሄድ ስለሚያደርግ የማስታወስ ችግርና የትኩረት ማጣትን ያስከትላል፡፡
  5. የሰውነት አካል እብጠት፤ የኩላሊት ጉዳት በሰውነታችን የሚገኙ ፈሳሾች በአግባቡ እንዳይወገዱ ስለሚያደርግ በሰውነታችን የተለያዩ ክፍሎች እብጠት ሊያስከትል ይችላል፡፡ በተለይም እግር፣ መገጣጠሚያና ፊት ላይ እብጠት ሊከሰት ይችላል፡፡
  6. የሰውነት መዛል፤ የኩላሊት ጉዳትን ተከትሎ የቀይ ደም ህዋስ ቁጥር ስለሚቀንስ የሰውን ማዛልን ጨምሮ የአዕይምሮና የጡንቻዎች ችግር ሊያጋጥም ይችላል፡፡
  7. የቆዳ አለርጂ፤ የኩላሊት ጉዳትን ተከትሎ በሰውነታችን የመርዛማ ንጥረ ነገሮች ክምችት ስለሚጨምር የቆዳ አለርጂ ሊያጋጥም ይችላል፡፡
  8. የኩላሊት አከባቢ ህመም፤ የኩላሊት እንፌክሽን ኩላሊት አከባቢ ህመም እንዲሰማ ያደርጋል፡፡
    ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች የኩላሊት ጉዳት ችግር ሊሆን ስለሚችል ኩላሊቶን በመመርመር ሊታደጉት ይገባል ይላል የናሽናል ኪድኒ ፋውንዴሽን መረጃ

ምንጭ፦Mahdere Tena

Advertisement