ታዋቂው ሳይንቲስት ስቴፈን ሆውኪንግ አረፈ

                                        

ዕለተ ረቡዕ መጋቢት 5 ቀን ጠዋት ላይ ታዋቂው እንግሊዛዊ የፊዚክስ ሊቅ ስቴፈን ሆውኪንግ በ76 ዓመቱ ካምብሪጅ በሚገኘው ቤቱ እስከወዲያኛው ያሸለበው።

‘ብላክ ሆልስ’ እንዲሁም ‘ሪላቲቪቲ’ ወይንም የንፅፅር ሕግ በተሰኙ ስራዎቹ የሚታወቀው የፊዚክስ ሊቁ ሆውኪንግ በርካታ ሳይንሳያዊ ፅሁፎችን አሳትሟል።

ገና በ22 ዓመቱ ሞተር ኒውሮን በተባለ በሽታ የተጠቃው ሆወኪንግ የመኖር ተስፋው እጅግ የመነመነ እንደሆነ ተነግሮት ነበር። ሆውኪንግ በሕይወት ቢቆይም በሽታው ሰውነቱን አሽመድምዶት ተንቀሳቃሽ ወንበር ላይ እንዲውል አደረገው።

“በጣም የምንወደው አባታች በማረፉ ከባድ ሃዘን ተሰምቶናል” ሲሉ ሉሲ፣ ሮበርትና ቲም የተሰኙት ልጆቹ ተናግረዋል።

ሆውኪንግ አንድ ወቅት ላይ “ለሚዱት ሰው መኖሪያ ካልሆነ ‘አጽናፈ ሰማይ’ (ዩኒቨርስ) ምንስ ዋጋ ይኖረዋል” ሲል ተናግሮ እንደነበር አይዘነጋም።

ፕሮፌሰር ሆውኪንግ በኮዝሞሎጂ ፅንሰ ሃሳብን ለንፅፅር ሕግ እና ኳንተም ሜካኒክስ ጥምረት በማዋል የመጀመሪያው ሰው ነው። ልቆም ሆውኪንግ ራዲያሽን በሚባለው ፅንሰ ሃስብም ይታወቃል።

ሆውኪንግ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በመቅረብ በሚናገራቸው ንግግሮቹ የሚታወቅ ሲሆን ‘ቲየሪ ኦፍ ኤቭሪቲንግ’ የተሰኘው ፊልም የሊቁን የፍቅር እና ምርምር ሕይወት ቁልጭ አድርጎ እንዲያሳይ ተደርጎ ተሰርቷል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement