“ተባረሃል” የነጩ ቤተ-መንግሥት ፖለቲካዊ ድራማ

                                       

ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እያደረጉ የነበሩት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ጉብኝታቸውን በአጭር አቋርጠው ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኋላ ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል።

ባለፈወ ዓመት በራሳቸው በፕሬዚደንት ትራምፕ ተመልምለው ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት ከገቡ ጊዜ አንስቶ ጀምሮ አወዛጋቢ ጉዳዮች ያልተለይዋቸው ቲለርሰን ከስልጣን መነሰታቸውን የተረዱት ከትራምፕ የትዊተር ገፅ ላይ ነበር።

ትራምፕ ቲለርሰን መባረራቸውን ባሳወቁበት ፅሁፍ በምትካቸው የሲአይኤው አለቃ ማይክ ፖምፔዎ መሾማቸውን አስፍረዋል።

ጥቁሮችን በድለዋል ተብለው የሚታሙት ጂና ሃስፕል ደግሞ የሲአይኤን መንበር ከፖምፔዎ ተረክበዋል።

ከስልጣን መውረዳቸውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ቲለርሰን ትራምፕንም ሆነ ፖሊሲያቸውን ከማሞገስ ተቆጥበው ተስተውለዋል።

ከቻይና እና ሰሜን ኮሪያ ጋር ጥሩ ስምምነት ላይ መደረሱ ትልቅ እመርታ መሆኑን ያወሱት ቲለርሰን በመግለጫቸው ወቅት ትንፋሽ ሲያጥራቸው ተስተውለዋል።

“ከቲለርሰን ጋር ያለኝ አለመግባባት ወደ ግላዊ ደረጃ ላይ ደርሷል” በማለት ለጋዜጠኞች የተናገሩት ትራምፕ በትዊተር መልዕክታቸውን “ቲለርሰንን ለአገልሎቱ እናመሰግናለን” ሲሉ አስፍረዋል።

ቲለርሰን ከትራምፕ አስተዳደር ራሳቸውን ካገለሉ እንዲሁም በፕሬዝደንቱ ከተባረሩ በርካቶች ተርታ እንዲሰለፉም ሆነዋል። ቲለርሰን ከነጩ ቤተ መንግሥት ሰዎች ጋር ቁርሾ ውስጥ እንደገቡ መዘገብ ከጀመረ ሰንበትበትም ብሏል።

ቲለርሰን በኢራን ጉዳይ እንዲሁም በሌሎች በርካታ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች መስማማት አለመድረሳቸው ሲዘገብ ቆይቷል። አልፎም ትራምፕን ‘ደደብ’ ብለህ ተሳድበሃል በሚል ክስ መግለጫ እንዲሰጡም ተደርገው ነበር።

ተተኪው ማይክ ፓምፔዎ ቦታውን እስኪረከቡ ድረስ የቲለርሰን ምክትል የሆኑት ጆን ሱሊቫን እስከ አውሮፓውያኑ ማርች 31 ድረስ ኃላፊነቱን እንደሚረከቡም ታውቋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement