ሞ ፋራህ የዘር ጥቃት ደረሰበት – Mo Farah Was Racially Abused at Munich Airport

                                     

 

አራት ጊዜ የኦሊምፒክ አሸናፊ የሆነው ሰር ሞ ፋራህ በጀርመን ሃገር አየር ማረፍያ ከጥበቃዎች የዘር ጥቃት ደርሶበታል።

በመጪው ወር ለሚካሄደው የለንደን ማራቶን ልምምድ ለማድረግ የ34 ዓመቱ እንግሊዛዊው ከሙኒክ ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዝ ነበር ይህ የተከሰተው።

በሶማሊያ የተወለደው አትሌት ሞ ፋራህ በኢንስታግራም አካውንቱ ይህን ግጭት የሚያሳይ ቪድዮ ለጥፏል።

”ሰውየው እንደጉድ እየነካካኝ ነው ። ይህ ግልጽ ጥቃት ነው። ግልጽ የሆነ ጥቃት ነው” ሲል ሞ ፋራህ ይታያል።

ቆየት ብሎም የ47 ሰከንድ ቪድዮ በማህበራዊ አካውንቱ ላይ ለጥፎ ”በ2018 እንደዚህ ዓይነት የዘር ጥቃት ማየት ያሳዝናል” የሚል ጽሑፍ ከሥሩ አስፍሯል።

ለስፖርት ፕሬስ አሶሴሽን በሰጠው መግለጫ ላይም የሞ ፋራህ ቃል አቀባይ ”በዛሬው ቀን ሞ ፋርህ ወደ ኢትዮጵያ ለልምምድ በሚጓዝበት ጊዜ በጀርመን አየር ማረፍያ ላይ ችግር ተከስቶ ነበር” ብሎ ተናግሯል።

በመቀጠልም ”ይህ ክስተት በዘር የተነሳሳ እንደሆነና የአይር መረፍያ ሠራተኞቹ ተገቢ ባልሆነ መልኩ እንደተቀበሉት ነው ሞ ፋራህ የተሰማው” ብሏል።

ሞ ፋራህ ከወር በኋላ በለንደንን ማራቶን ከመሳተፉ በፊት ባለፈው እሁድ ‘ቢግ ሃፍ’ የተሰኘውን ሩጫ አሽንፎ ነበር።

ቢቢሲ ስፖርት የሙኒክን አይር ማረፍያ ባለሥልጣኖችን ለማነጋገር ሞክሯል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement