እንግሊዝ በኢራቅና ሶሪያ የአየር ድብደባዎች 1 ነጥብ 75 ቢሊየን ፓውንድ ማውጣቷ ተነገረ – UK Spent £1.75 Billion on Airstrikes in Iraq, Syria Since 2014

                                  

እንግሊዝ እንደ አሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2014 ጀምሮ በአሜሪካ መራሹ ዘመቻ በሶሪያና ኢራቅ አይ ኤስ ላይ በወሰደችው የአውሮፕላንና ድሮን ጥቃት 1 ነጥብ 75 ቢሊየን ፓውንድ ወጪ ማድረጓን ድሮን ዋር የተሰኘ ተቋም ገለፀ።

 የንጉሳዊ የአየር ሀይል ቶርናዶ፣ ታፎንና ሌሎች የጦር አውሮፕላኖች በመጠቀም እንደ አሮፓውያኑ አቆጣጠር ከነሃሴ 2014 ጀምሮ 42 ሺህ ሰዓታት ወይም አምስት አመታት ያክል በአየር ላይ እንደቆዩ ነው ሪፖርቱ ያመለከተው።

በዚህም በአየር ድብደባ ብቻ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ፓውንድ ወጪ ሆኗል ነው የተባለው።

ታፎንና ቶርናዶ የተሰኙት የጦር አውሮፕላኖች በሰዓት 80 እና 35 ሺህ ፓውንድ የሚገመት ወጪ ማድረጋቸው ነው የታወቀው።

በሪፖርቱ የአብራሪዎች፣ የነዳጅ፣ የጥገና እና የካፒታል ወጪ እንዳልተካተተ ታውቋል።

ባላለፉት ሶስት ዓመታት 1 ሺህ 700 የአየር ድብደባዎችን የንጉሳዊ የአየር ሀይል በሶሪይና ኢራቅ እንደፈፀመ እና 268 ሚሊየን ፓውንድ የሚገመት የጦር መሳሪያ መጠቀሙ ተነግሯል።

በአየር ጥቃቱ 3 ሺህ 345 ቦንቦችና ሚሳኤሎችም ጥቅም ላይ ውለዋል።

በተጨሪም እጅግ ውድ የሚባለውን የኩሩስ ሚሳኤል በመጠቀም 6 ነጥብ 4 ሚሊየን ፓውንድ ወጪ ማድረጓ ነው የሚነገረው።

ተቋሙ ሪፖርቱ በሶሪያና ኢራቅ የተወሰደውን የአየር ጥቃት ብቻ የሚመለከት እንደሆነ ቢናገርም።

መንግስት በበኩሉ በሶሪያና ኢራቅ በተወሰደው እርምጃ አጠቃላይ ወጪው 779 ሚሊየን ፓውንድ እንደሆነ ሲናገር ሪፖ ርቱን ያወጣው ተቋም መንግስት አጠቃላይ ወጨውን አላካተተም ብሏል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement