የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ

                                                         

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ።

በሃገሪቷ የተከሰተውን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ለመቀልበስ የሚንስትሮች ምክር ቤት ከዛሬ ጀምሮ የሚተገበር የአስቸኳይ ጊዜ ማወጁን አስታወቀ።

አዋጁ የዜጎች ዴሞክራሲያዊ እና ፖለቲካዊ መብቶች ላይ ገደብ ይጥላል የሚል ስጋት ፍጥሯል።

በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 93 መሰረት የሚንስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ይችላል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አተገባበር በሚመለከት ዝርዝር መረጃ ቅዳሜ የካቲት 10 ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የሚንስትሮች ምክር ቤት ዓርብ ከሰዓት መግለጫ እንደሚሰጥ ተገልጾ ሲጠበቅ ቢቆይም፤ ከስድስት ሰዓታት ቆይታ በኋላ ለጋዜጠኞች የተባለው መግለጫ ሳይሰጥ ቀርቶ አንዲበተኑ ተደርጎ ነበር።

ምሽት ሁለት ሰዓት ላይ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ያለ ተጨማሪ ማብራሪያ አዋጁ እንደታወጀ ዘግበዋል።

ከአንድ ዓመት ቀደም ብሎ ለዘጠኝ ወራት የዘለቀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመላው ሃገሪቱ ተግባራዊ እንደነበር ይታወሳል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement