የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለ6 ወራት እንሚቆይ ተገለጸ

                               

አርብ ምሽት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለስድስት ወራት የሚቆይ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ አስታወቁ::

የሚኒስትሮች ምክር ቤትም ውሳኔውን በሙሉ ድምፅ እንደተቀበለውና: በሃገሪቱ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት የሽግግር መንግሥት ማቋቋም አስፈላጊ እንዳልሆነ ሚኒስትሩ ተናግረዋል::

በሃገሪቱ ያለው የፀጥታ ችግር እየተባባሰ መሆኑን ዛሬ ቅዳሜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተናገሩት ሚኒስትሩ ችግሩ በዋና ከተማዋ በአዲስ አበባም መንፀባረቁን ገልፀዋል::

ሚኒስትሩ እንዳሉት ኢህአዴግ ለ17 ቀናት ባደረገው ግምገማ ላይ ያለው ችግር በ15 ቀናት ውስጥ ካልተፈታ የአስቸኳይ ጊዜ ሊታወጅ እንደሚችል ቀደም ሲል ከስምምነት ላይ ተደርሶ እንደነበር ጠቁመዋል::

ለስድስት ወራት የሚቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በየጊዜው የሚገመገም ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ከተገፕ ለአራት ወራት ሊራዘም እንደሚችልም ተገልጿል::

አዋጁ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብ የተናገሩት ሚኒስትር ሲራጅ: የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚከታተል ኮማንድ ፖስት ተቋቁሟል::

ኮማንድ ፖስቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ እንደሆነም ተገልጿል::

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement