በታይዋን የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እስካሁን አራት ሰዎችን ገድሏል – Taiwan Earthquake: Series of Powerful Aftershocks Hit Hualien

                                     

በታይዋን በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ እስካሁን የአራት ሰዎች ህይዎት አልፏል።

በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 4 የተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ፥ ሁዋሊየን በተሰኘችው የደሴቲቱ ምስራቃዊ ክፍል የደረሰ ነው ተብሏል።

በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪ ከ200 በላይ ሰዎች መጎዳታቸውም ተነግሯል፤ በርካታ ሰዎችም የገቡበት አልታወቀም።

የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት ከስፍራው 160 ኪሎ ሜትር በምትርቀው መዲናዋ ታይፔይ ተሰምቷልም ነው የተባለው።

በአደጋው ሳቢያም በርካታ ህንጻዎች ሲፈራርሱ የከተማዋ የፍጥነት መንገዶችም አገልግሎት መስጠት አቁመዋል።

በከተማዋ በተለይም ሆስፒታሎች በአጋው ሳቢያ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግደዋል ነው የተባለው።

የመሬት መንቀጥቀጡ ያስከተለው ጉዳት 40 ሺህ መኖሪያ ቤቶችን ያለ መጠጥ ውሃ ማስቀረቱንም መረጃዎች ያመላክታሉ።

ከመሬት መንቀጥቀጡ በኋላ የከተማዋ አብዛኛው ክፍል ከፍተኛ ጉዳት ማስከተሉም ተነግሯል።

ከሁለት አመት በፊት ታይናን በተሰኘችው ከተማ በደረሰ ተመሳሳይ አደጋ በጥቂቱ 116 ሰዎች መሞታቸው ይነገራል።

በታይዋን በዚህ ወር ብቻ በሃገሪቱ ከ100 በላይ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች ተከስተዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement